1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግድቡ ውኃ ሙሌት እና ቀጣዩ ድርድር 

ሰኞ፣ ሐምሌ 12 2013

ለኃይል ማመንጫ የሚያገለግሉ ሁለት ተርባይኖች ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልገው የውኃ መጠን በታላቁ የኅዳሴ ግድብ መጠራቀሙን የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ምኒስትሩ ስለሺ በቀለ ይፋ አድርገዋል። "ሁለቱ ተርባይኖች ኃይል እንዲያመነጩ ብርቱ ስራዎች እየተሰሩ ነው። ያንን በቅርብ ወራት በማጠናቀቅ ልፋታችንን ውጤት ላይ እናደርሳለን" ብለዋል።

https://p.dw.com/p/3whFt
BG Grand Renaissance Dam | Äthiopiens Minister für Wasser, Bewässerung und Energie, Seleshi Bekele
ምስል AFP/M. Tewelde

የግድቡ ውኃ ሙሌት እና ቀጣዩ ድርድር 

ኢትዮጵያ የሁለተኛውን ዓመት የሕዳሴ ግድብ ሙሌት አገባዳ ውኃው በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ መጀመሩን የውኃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ይፋ አደረጉ።
ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ይህ ውጤት 2 ተርባይኖችን ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልገው የውሃ መጠን እንደሆነና እዚህ ደረጃ ለመድረስም በዓመቱ መጠነ ሰፊ ሥራ ተከናውኗል ማለት ነው ብለዋል።

ሁለቱ ተርባይኖች እንዲያመነጩ ብርቱ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሩ ያንንም በቅርብ ወራት በማጠናቀቅ ውጤት ላይ እናደርሳለን በማለት አረጋግጠዋል።
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የግድቡ ተደራዳሪ የውኃ ሙሌቱ ሂደት ግብፅም ሱዳንም በጎርጎርያኑ 2015 የፈረሙት መሆኑን አስታውሰው አሳሪ ውል እንያዝ የሚለው ጥያቃያቸውም የማያስኬድ እንደሆነ ገልፀዋል።

ሰለሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ