1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋዜጠኞች እስራትና የመገናኛ ብዙኃን ማኅበር ስጋት

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 6 2014

ከሰሞኑ በሕግ ጥላ ሥር እንዲውሉ የተደረጉ ጋዜጠኞች የሚገኙበት ሁኔታ በቤተሰቦቻቸው እንዲታወቅ አለመደረጉን እንደሚያወግዝ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ማኅበር ተናገረ። ኢትዮጵያ የምትገኝበትን ወቅታዊ ሁኔታ እገነዘባለሁ ያለው ማኅበሩ ጋዜጠኞች በትክክል ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ለእሥር መዳረጋቸው እንዳሰጋው አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/44J3a
Äthiopien | EMMPA Logo
ምስል EMMPA

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ማኅበር የታሰሩ ጋዜጠኞች የት እንዳሉ አለመታወቁ አሳስቦኛል አለ

ከሰሞኑ በሕግ ጥላ ሥር እንዲውሉ የተደረጉ ጋዜጠኞች የሚገኙበት ሁኔታ በቤተሰቦቻቸው እንዲታወቅ አለመደረጉን እንደሚያወግዝ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ማኅበር ተናገረ።
ኢትዮጵያ የምትገኝበትን ወቅታዊ ሁኔታ እገነዘባለሁ ያለው ማኅበሩ ጋዜጠኞች በትክክል ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ለእሥር መዳረጋቸው እየተስተዋለ ነበር ያለው የጋዜጠኝነት ትግበራ ነፃነት ላይ ጥላ እንዳያጠላበት ሥጋት ፈጥሯል ብሏል።
ማኅበሩ ጋዜጠኞቹ ፍትሕ እንዲያገኙ ፣ የሕግ ድጋፍ የማግኘት መብታቸውም እንዲጠበቅና ቤተሰቦቻቸውም ጋዜጠኞቹን የመጠየቅ መብታቸው እንዲከበር ጠይቋል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የውጭ መገናኛ ብዙኃን የተዛቡ እና ሚዛናዊነት የጎደላቸው ዘገባዎች እየተሰራጩ መሆኑን ተመልክቻለሁ ያለው ማኅበሩ መገናኛ አውታሮቹ ከዚህ መሰሉ ዘገባ እንዲወጡም ጠይቋል።
በሌላ በኩል በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር እንዲያድግ ፣ ሙያውም በመርሁ መሰረት እንዲተገበር ዘርፉን የተመለከተ አገር አቀፍ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።
ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመታት በፊት የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀንን አዲስ አበባ ላይ አክብራ የነበረ ሲሆን በወቅቱ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲ ፒ ጄ ኢትዮጵያን ለመጀመርያ ጊዜ ጋዜጠኞች ያልታሰሩባት አገር በሚል ጠቅሷት ነበር።
የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅቱ ከቀናት በፊት ባወጣው የ2021 ዓ.ም ዘገባው ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት ሁለተኛ ናት ብሏል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ