በድንበር ከተሞች ቀኝ አክራሪዎች ቅስቀሳ አጧጡፈዋል
ዓርብ፣ መስከረም 5 2010ማስታወቂያ
አምስቱ የዶይቼ ቬለ የአፍሪቃው ክፍል ጋዜጠኞች ትላንት እና ዛሬ ረፋዱን ጀርመን እና ፖላንድ ድንበር ነበሩ፡፡ ፍራንክፋርት ኦደር በተሰኘችው የድንበር ከተማ መግቢያ ድልድይ አጠገብ በጀርመንኛ የተፃፈው የቅስቀሳ ወረቀት "እስልምና የጀርመን አካል አይደለም" በሚል ይነበባል፡፡ ቀኝ አክራሪው መጤ ጠሉ አማራጭ ለጀርመን (AFD) የተሰኝው ፓርቲ ለምርጭ ቅስቀሳ ከሚጠቀምባቸው መፈክሮች አንዱ ነው፡፡በፍራንክፉርት ኦደር ከተማ ውስጥም በብዛት የሚታዩት የዚሁ AFD ፖርቲ የቅስቀሳ ወረቀቶች ናቸው፡፡ ሰኞ እለት ባልደረባችን ኮተን ከተማ ውስጥ ያናገራቸው የግራዎቹ ፖርቲ አንድ እጩ "የመለያያ ግንብ ሳይሆን የመቀራረቢያ ድልድይ ልንገነባ ይገባል" ብለው ነበር፡፡ በትላንት እና ዛሬ ውሎው እንደዚሁም በአጠቃላይ የምርጫ ዘመቻው ስለተመለከታቸው ጉዳዮች ያካፈለንን መረጃ ለማድመጥ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡፡
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ተስፋለም ወልደየስ
ኂሩት መለሰ