የጀርመን ቅኝ ግዛት አስከፊ ታሪክ ቅሪት
ሰኞ፣ መጋቢት 9 2016ማስታወቂያ
አውሮጳውያን ከግዛታቸው በብዙ እጥፍ የሚበልጠውን የአፍሪቃ አህጉር ቅኝ የገዙበት መንገድ አስገራሚ ነው ። እያንዳንዱ ሀገር ወደ አፍሪቃ እግሩን ያስገባበት የታሪክ አጋጣሚም እንዲሁ አስገራሚ ነው። በዚህ ረገድ ጀርመን በርካታ የአፍሪቃ ሃገራትን ቅኝ የገዛችበት አጋጣሚ በግለሰቦች ፍላጎት ላይ የተመሰረተ እንደነበር ሲታሰብ በእርግጥ ያስገርማል። አንድ ጀርመናዊ ነጋዴ መሬት በመግዛት በትንሹ የጀመሩት የመሬት መቀራመት የማታ ማታ የሃገሪቱን መንግስት ስቦ በማስገባት በርካታ የምስራቅ እና የደቡብ ምዕራብ እና የምራዕራብ አፍሪቃ ሃገራትን ቅኝ አስገዝቷል። በነዚህ የቅኝ ግዛት ዘመናት ጀርመናውያኑ በአፍሪቃውያኑ ላይ ታሪክ የማይረሳውን ግፍ ፈጽመዋል። የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል፤ ማህበረሰቦች ያለፍላጎታቸው ተከፋፍለዋል፤ ተሰደዋል፤ ሰዎች እንደእንስሳ በፓርኮች ውስጥ ለእይታ ቀርበዋል። የጀርመን ቅን ግዛት አስከፊ ታሪክ ቅሪት ጀርመን ቅኝ በገዛቻቸው ታንዛንያ ፣ ቦትሰዋና ፣ ካሜሩን ፣ ቶጎ እና ሌሎችም የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪቃ ሃገገራት የቅኝ ግዛት ዘመን አስከፊ ታሪኮች ይቀርቡበታል።#የጀርመን ቅኝ ግዛት አስከፊ ታሪክ #Shadows of German colonialism
ጸሐፊ ፤ ካይ ኔቤ
አዘጋጅ ፤ ታምራት ዲንሳ