1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ላይ ንግድ

ዓርብ፣ ጥቅምት 23 2011

ሁለቱን ሐገራት በየብስ የሚያገናኙ የአዋሳኝ ድንበር መተላለፊያዎች ባለፈዉ መስከረም አንድ ከተከፈቱ ወዲሕ የድንበር አካባቢ የንግድ ልዉዉጥ ተጠናክሯል።ሸቀጦቻቸዉን ከአንዱ ሐገር ወደሌላዉ እየወሰዱ የሚሸጥኑ እና ከሌላዉ ሐገር የሚገዙ ነጋዴዎች ጥሩ የሥራ እድል እንደተፈጠረላቸዉ ይናገራሉ

https://p.dw.com/p/37ZkJ
Äthiopien Addias Ababa - Isaias Afwerki - Abiy Ahmed
ምስል picture-alliance/AP Photo/M. Ayene

(Beri.Mekele) Ethio-Eritrea Border Trade - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መሪዎች ባለፈዉ ዓመት ዓመት ማብቂያ የሠላም ሥምምነት ከተፈራረሙ ወዲሕ የተጀመረዉ የሁለቱ ሐገራት የሕዝብ ለሕዝብ እና የንግድ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እና እያደገ ነዉ።በተለይ ሁለቱን ሐገራት በየብስ የሚያገናኙ የአዋሳኝ ድንበር መተላለፊያዎች ባለፈዉ መስከረም አንድ ከተከፈቱ ወዲሕ የድንበር አካባቢ የንግድ ልዉዉጥ ተጠናክሯል።ሸቀጦቻቸዉን ከአንዱ ሐገር ወደሌላዉ እየወሰዱ የሚሸጥኑ እና ከሌላዉ ሐገር የሚገዙ ነጋዴዎች፤ ለመቀሌዉ ዘጋቢያችን እንደነገሩት፤ ጥሩ የሥራ እድል ተፈጥሮላቸዋል ።ይሁንና የምጣኔ ኃብት አዋቂዎች እንደሚሉት ግብር የማይከፈልበት፤ የሸቀጦች ጥራት፤ ይዘትና ብዛት የማይወሰንበት ከሁሉም በላይ ሕጋዊ ሥርዓት ያልተበጀለት የንግድ ልዉዉጥ የሁለቱን ሐገራት ምጣኔ ሐብት ሊጎዳ፤ ምናልባትም የጥቅም ግጭት ሊያስከትል ይችላል።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ