1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዴምህት የቀድሞ ታጋዮች ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናገሩ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 2 2012

በኢትዮጵያ ከተደረገው የፖለቲካ ለውጥ በኋላ ከኤርትራ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት የቀድሞ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ (በትግርኛ ምህፃሩ ዴምህት) ታጋዮች በመንግስት ቃል የተገባላቸው ድጋፍ ባለማግኘታቸው ችግር ላይ መውደቃቸው ለዶይቼ ቬለ ገለፁ፡፡ የቀድሞ የዴምህት ታጋዮቹ ፓርቲያቸው በከፍተኛ አመራሩ 'በሕገወጥ መንገድ ከስሞ' ወደ ህወሓት መቀላቀሉም ተቃውመዋል። የኢትዮጵያ መንግስትን በሐይል ለመጣል ለዓመታት በኤርትራ በረሐ ሆኖ ይታገል የነበረው ዴምህት፣ በ2011 ዓ.ም ወርሐ መስከረም የኢትዮጵያ መንግስት ባደረገው ጥሪ መሰረት ከሁለት ሺህ በላይ ሽምቅ ተዋጊዎች ይዞ መመለሱ ይታወሳል። ቪዲዮ፦ ሚሊዮን ኃይለስላሴ

https://p.dw.com/p/3dXht