1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዳንካሊያ የራስ ገዝ ጥያቄ

እሑድ፣ ሰኔ 23 2016

"ዋናው የጉባዔያችን ራስ ገዝ ዳንካሊያ ውስጥ ደንካሊያ የሚባል ዘጠኝ ወይም ስምንት ቦታ ይከፈላል የኤርትራ ክልሎች ማለት ነው። የራሳችንን መብት ራሳችን የምናስከብርበት ራስ ገዝ በሚባል ቦታ ላይ እንድናገኝ በሚል ጉባኤ ላይ ይህን ጉባኤ ያደረግንበት ዋናው ይሄ ነው።"

https://p.dw.com/p/4hgbb
Eritrea Eritrean Afar National Congress meeting in Canada
ምስል Tariku Hailu/DW

የዳንካሊያ የራስ ገዝ ጥያቄ

የኤርትራ ዓፋር ብሔራዊ ኮንግረስ ጉባዔ በካናዳ 

የኤርትራ ተቃዋሚው የዓፋር ብሔራዊ ኮንግረስ በሃገሪቱ ለዳንካሊያ  ግዛት የራስ ገዝ አስተዳደር መብት እንዲከበር ጥሪ አቀረበ።

የተቃዋሚ ድርጅቱ ጥሪውን  ያቀረበው፣ ስድስተኛ ዓመታዊ ጉባዔውን፣ በኦታዋ ካናዳ ለሁለት ቀናት ባካሄደበት ወቅት ነው።

የኤርትራ ዓፋር ብሔራዊ ኮንግረስ(ኤኤንሲ) ስድስተኛ ዓመታዊ ጉባኤውን፣ትናንትና እና ከትናንትና በስቲያ በኦታዋ ካናዳ አካሄዷል።

 ድርጅቱ፣ በስደት ላይ ያለናበኤርትራ ዳንካሊያ የሚኖሩ የዓፋር ተወላጆችን መብት ለማስከበር የሚንቀሳቀስ መሆኑን የኮንግረሱ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና ቃል አቀባይ አቶ አሊ መሐመድ ዑመር ለዶይቸ ቨለ ገልጸዋል።

የአፋር ብሔራዊ ኮንግረስ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና ቃል አቀባይ አቶ አሊ መሐመድ ዑመር
የአፋር ብሔራዊ ኮንግረስ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና ቃል አቀባይ አቶ አሊ መሐመድ ዑመር ምስል Tariku Hailu/DW

የዳንካሊያ የራስ ገዝ ጥያቄ

ቃል አቀባዩ እንዳሉትም፣የጉባዬው ዋነኛ ትኩረት የዳንካሊያ የራስ ገዝ አስተዳደር መብት ጥያቄ ነው። "ዋናው የጉባዔያችን ራስ ገዝ ዳንካሊያ ውስጥ ደንካሊያ የሚባል ዘጠኝ ወይም ስምንት ቦታ ይከፈላል የኤርትራ ክልሎች ማለት ነው። የራሳችንን መብት ራሳችን የምናስከብርበት ራስ ገዝ በሚባል ቦታ ላይ እንድናገኝ በሚል ጉባኤ ላይ ይህን ጉባኤ ያደረግንበት  ዋናው ይሄ ነው።ራስ ገዝ የማግኘት መብት እንዲከበርልን የሚል ለዓለም ዓቀፍ ማኀበረሰብ የምንልከው መልእክት ይኖራል።ለሚዲያም የምንልከው መልዕክት ይኖራል። ለመንግስታቱ ድርጅት፣ኢንዲጂኒየስ ሕዝቦች የሚባልም ድርጅትም አለ ለእነሱም እንልካለን። ስለዚህ ዋናው የራስ ገዝ መብታችንን እንዲከበርልን በሚል ነው።"

የሰብዓዊ መብት ረገጣ 

እንደ አቶ አሊ ገለጻ፣የራስ ግዛት ጥያቄውን ማንሳት ያስፈለገው፣በኤርትራ በሚኖሩ የዓፋር ህዝቦችላይ፣ሃገሪቱን በሚያስተዳድረው  ገዢ ፓርቲ የሚደርሰው የሰብአዊ መብት ረገጣ እና የምጣኔ ሀብት ጭቆና አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ነው።

"እኛ ደግሞ በሀገራችን ላይ፣ሃያ ዘጠኝ ሠላሳ ዓመት በጣም የተጎዳን ሕዝብ ስለሆንን፣በጣም ደግሞ 75 ከመቶ ሃገር ለቆ የወጣበት ህዝብ ነው።ከሃገሪቱ ኤኮኖሚም ከሃገሪቱ ፖለቲካ፣ከሃገሩ ያለውን በሙሉ በዘዴ ከሃገር እንድንወጣ ያደረገው የሻዕቢያ መንግስት ያደረገው፣ ግፍና እና በደል እስከዛሬ ድረስ ስንቋቋምና ስንቃወም ነበር።"

የኤርትራ ዓፋር ብሔራዊ ኮንግረስ ጉባዔ በካናዳ
የኤርትራ ዓፋር ብሔራዊ ኮንግረስ ጉባዔ በካናዳ ምስል Tariku Hailu/DW

በኤርትራ የሚኖሩ የዓፋር ህዝቦችን መብት ለማስከበር ስለተደረገው እንቅስቃሴ ሲያስረዱም፣ቃል አቀባዩ የሚከተለውን ብለዋል።

" መብታችንን እንዴት ማስከበር እንችላለን በማለት፣ ኤክስፐርቶችንም የዓለም ኤክስፐርቶችንም ሆነ የዓለም አቀፉን ማኀበረሰብ ጭምር ብዙ ስንከራከር ብዙ ስንወያይ ቆይተናል።"

የፖለቲካ ድርጅታቸው፣ የኤርትራ ዓፋር ብሔራዊ ኮንግረስ(ኤኤንሲ) ከሌላ ፓርቲ ጋር የውህደት ስምምነት በመፍጠር የተቋቋመና፣በተለያዩ ቦታዎች ቅርንጫፎች እንዳሉትም ከቃል አቀባዩ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።

"እኛ በሌላ ስም የኤርትራ ዓፋር ግዛት በስደት በሚል ተቋቁመን ነበር፣ በኋላ ደግሞ አንድ የዓፋር ድርጅት ነበር።ከእርሱ ጋር ተቀላቅለን፣የኤርትራ ዓፋር ብሔራዊ ኮንግረስ በ 2018 ስዊዲን ኦፕሳላ ላይ አቋቋምን። ዋና መስሪያ ቤታችን ያለው እዚሁ ጉባዔ በምናደርግበት ካናዳ ኦታዋ ነው። ግን አውሮፓ ውስጥ አለ፣አሜሪካ ውስጥ ቅርንጫፎች እስከ ጂቡቲ፣ኢትዮጵያ ሳዑዲ አረቢያ ቅርንጫፎች አለን፤ ኢትዮጵያ አባላቶች አለን።"ብለዋል።
ታሪኩ  ኃይሉ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር