1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል

ረቡዕ፣ ጥቅምት 24 2014

የደቡብ ክልል ምክር ቤት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የፌዴራሉ 11ኛ ክልል ሆኖ እንዲደራጅ የሚያስችለውን የሥልጣን ርክክብ አካሄደ ። የሥልጣን ርክክቡን የተደረገው ዛሬ በሀዋሳ ከተማ በተካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ነው ። ምክር ቤቱ ርክክቡን ያደረገው በህዝበ ውሳኔው አፈጻጸም ዙሪያ በቀረበለት ሪፖርት ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ነው ።

https://p.dw.com/p/42WaD
Süd Äthiopien Regional Council Meeting
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

የደቡብ ክልል መስተዳድር ከደቡብ ምዕራብ ክልል ጋር የስልጣን ርክክብ ማድረጉ

የደቡብ ክልል ምክር ቤት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የፌዴራሉ 11ኛ ክልል ሆኖ እንዲደራጅ የሚያስችለውን የሥልጣን ርክክብ አካሄደ ።

ምክር ቤቱ የሥልጣን ርክክቡን ያደረገው ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ባካሄደው 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት አስቸኳይ ጉባኤ ነው ።

ምክር ቤቱ ርክክቡን ያደረገው በህዝበ ውሳኔው አፈጻጸም ዙሪያ በቀረበለት ሪፖርት ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ነው ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ የካፋ ፣ የሸካ ፣ የዳውሮ ፣ የቤንች ሸኮ ፣  የምዕራብ ኦሞ እና የኮንታ ልዩ ወረዳ ራሳቸውን ችለው በክልልነት ለመደራጀት የሚያስችላቸውን የሕዝበ ውሳኔ ድምፅ የሰጡት ባለፈው መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ነበር።

በህዝበ ውሳኔው ድምፅ ከሰጡት 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን መራጮች መካከል ከ98 በመቶ በላይ የሚሆኑት ከደቡብ ክልል በመነጠል የጋራ ክልል መመሥረትን ደግፈው ድምፅ መስጠታቸውን የኢትዮጲያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል ።

በሕዝበ ውሳኔው ድምፅ ውጤት መሰረት አምስቱ ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ በቀጣዩ ሳምንት የጋራ ያሉትን ክልል ያዋቅራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ታምራት ዲንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ