1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩጋንዳ የፖለቲካ ውጥረት

ሐሙስ፣ መስከረም 10 2011

የዩጋንዳ ፖሊስ ለህክምና ከሀገር ውጭ ሰንብተው ዛሬ ወደ ሀገር ቤት የተመለሱትን ተቃዋሚ የምክር ቤት አባል በቁጥጥር ስር ማዋሉ በሀገሪቱ ውጥረት ቀስቅሷል።

https://p.dw.com/p/35FpG
Bobi Wine, der umstrittene Popstar aus Uganda, wurde Parlamentarier
ምስል DW/S.Schlindwein

ወጣቱ ፖለቲከኛ ቢቢ ዋይኒ

ከታዋቂ ሙዚቀኛነት ወደ ፖለቲካው የገቡት የ36 ዓመቱ የምክር ቤት አባል ሮበርት ካያጉላኒ ወይም አድናቂዎቻቸው እንደሚጠሯቸው ቦቢ ዋይኒ ለህክምና ከቆዩበት ዩናይትድ ስቴትስ ሲመለሱ ኢንቴቤ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በፖሊስ መያዛቸው ተገልጿል። ወጣቱ የምክር ቤት አባል እና የሙሴቪኒ ቀንደኛ ተቺ ግን በሀገሪቱ የፖለቲካ ለውጥ ሳይታይ የጀመሩትን ትግል እንደማያቆሙ ዝተዋል። ደጋፊዎቻቸው የሆኑት በርካታ የዩጋንዳ ወጣቶችም ለውጥ ፈላጊነታቸውን እየገለፁ ነው። ስለዩጋንዳ የፖለቲካ ውጥረት ከናይሮቢ ቻላቸው ታደሰን በአጭሩ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ቻላቸው ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ