1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩክሬን ጦርነት ለአውሮጳ ኅብረት ዳፋ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 27 2014

የአውሮጳ ኅብረት ሩስያ ዩክሬንን በመውረሯ የተነሳ መቀጣጫ በሚል ተደጋጋሚ ማእቀብ ጥለዋል። ማዕቀቦቹ ግን ጦርነቱን ማስቆም አልቻሉም። ጦርነነቱ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ የሞቱ እና ከዩክሬን የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው።

https://p.dw.com/p/4Asud
EU Ursula von der Leyen und Josep Borrell, PK zum Ukraine Krieg
ምስል Kenzo Tribouillard/AFP/Getty Images

ዩክሬንን እያወደመ ያለው የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት፤ በአውሮፓ ህብረት አገሮች ላይ ከደቀነው የደህንነት ስጋት አልፎ፤ ኢኮኖሚያቸውን ክፉኛ እይተፈታተነው ነው። ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ወደ ህብረቱ የገቡት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዩክሪኖችን የፈጠሩት የኢኮኖሚ ጫና እንዳለ ሆኖ፤ አሁን የጦርነቱ ጦስ በህብረቱ አገሮች አጠቃላይ ኢኮኖሚ ላይ ያስከተለው ተጽኖ በግልጽ እየታየ ነው። በሸቀጦች፣ ጋዝና ነዳጅ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሬ በመከሰቱ፤ በህብረቱ አገሮች ማህበራዊ ችግሮች ተስፋፍተዋል ፤ በርክታ የህብረተሰብ ክታፍሎችም የጦርነቱ መዘዝ ቀጥተኛ  ሰለባ ሁነዋል። 

ይሮ ስታት የተባለው የህብረቱ አገሮች የኢኮኖሚ እድገት መጠቋሚያ እንደገለጸው፤  ባለፈው የመጀመሪያው እሩብ ዓመት የፈረንሳይ ኢኮኖሚ ባለበት የቆመ ሲሆን የጣሊያን ደግሞ መቀነሱን አሳይቷል። የሌሎቹም አገሮች የኢኮኖሚ እድገት እንደዚሁ የቆመ ወይም የቀነሰ ሲሆን፤ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ባለፉት ሦስት ወራት የህብረቱ  ኢኮኖሚ በአጠቃላይ በ0.2 ክመቶ እንደቀነሰ መረጃው ያሳያል። ጦርነቱ የሚቀጥል ክሆነም በተለይ በጋዝና ነዳጅ ዋጋ የሚጨመር መሆኑን በመግለጽም፤ ባለፈው ሚያዚያ ወር ብቻ የአውሮፓ ህብረት ኢሮ ዞን የግሽበት መጠን 7.5 ከመቶ የደረሰ መሆኑ ተገልጿል።  የአውሮፓ ኢኮኖሚ ባለፉት አስርት ዓመታት ሁለት ግዜ ማለት ጎርጎረሳዉያኑ በ2008 እና በቅርቡ ደግሞ በኮቪድ ምክኒያት የኢኮኖሚ ቀውስ ገጥሞት የነበር መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ ይህ ጦርነት የህብረቱን ኢኮኖሚ ወደ ድቀት ውስጥ እንዳይገባ ያሰጋል ነው የሚባለው። 

የአውሮፓ ህብረት እንደገና ስድስተኛውንና ነዳጅና ጋዝን የሚጨምረውን ማዕቀብ በሩሲያ ላይ ለመጣል የወሰነ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህ ግን በሩሲያ ላይ ሊፈጥር ከሚችለው ጫና ባላነሰ ሁኒታ የሀብረቱን ኢኮኖሚም ሊጎዳው እንደሚችል  ነው የሚነገረው። የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝድንት ቮንዴር ላይን እንደሚሉት፤ ህብረቱ በሩሲያ ላይ ጫና ፈጣሪ እርምጃዎችን ሲወስድ  በህብረቱ ኢኮኖሚ ላይ የከፋ ችግር እንዳይከሰት ጥንቃቄ ይደረጋል። በሩሲያ ላይ ጫና ፈጣሪ እርምጃዎችን ስንወስድ በህብረቱና ሌሎች አጋሮቻችን ላይ ተመሳሳይ ችግር እንዳይደርስ ጥንቃቄ እናደርጋለን፤ ምክኒያቱም ዩክሬንን የበለጠ መርዳት የምንችለው ኢኮሚያችን ጠንካራ ሆኖ ሲቀጥል ነው ሲሉም ተሰማምተዋል። ሆኖም ግን በምን ሁኒታና እንዴት በተጨባጭ የህብረቱን ኢኮኖሚ ከተዛማጅ ጉዳት መከላከልና መጠበቅ እንደሚቻል ግልጽ አላድረጉም እየተባለ ነው። አንዳንድ አባል አገሮች ለምሳሌ እንደ ሀንጋሪና ስሎቫኪያ የመሳሰሉ፤ ህብረቱ ከሩሲያ ነዳጅ ዘይት መግዛትን ሊያቆም ሲወስን እንዴትና ከየት ክሩሲያ ይገኝ የነበረውን ነዳጅ ዘይት መተካት እንደሚቻል ግልጽ አላደረገም በማለት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው።፡ የማዕቀቡና በአጠቃላይ የጦርነቱ ወጭ በያገሮቹ ያለውን ማህበራዊ ችግር እያሰፋው መሆኑም በግልጽ እየታየ ሲሆን፤ ችግሩ እንደየአገሮቹ ሁኒታ ቢለያይም በሁሉም አባል አገሮች ግን እየተስፋፋ መሆኑ ታውቋል።

የጦርነቱ አስከፊነት ብቻ ሳይሆን መቆሚያውም የማይታወቅ መሆኑ፤ መጭውን ግዜ ለመተንበይ የማያስችል ሲሆን፤ እንደዚህ አይነቱ ሁኒታ ደግሞ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን  የሚገታና ቀውስም ሊያስከትል ይችላል በማለት ካሁኑ መጭው ግዜ የባሰ ሊሆን ላለመቻሉ ዋስትና የለም የሚሉ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ጥቂቶች ይደሉም። 

በዚሁ ጦርነት ሰበብ በተከሰተው የዋጋ መናር መክኒያት በአውሮፓም ብዙ መኖር ያቃታቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ያሉ መሆኑ እየተገለጸ ነው።፡ መንግስታት የአቅርቦት ችግሮችን ካልፈቱና  የደመወዝ ማስተካከያም ካላደረጉ በስተቀር ችግሩ እንደማይቃለል ነው  እንደ ዳቪድ ሪናልዲ የመሰሉ በማህብረሰብ ላይ የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች የሚናገሩት፤ መንግስት የዜጎችን የመግዛት አቅም ተመጣጣኝ በሆነ የደመወዝ ማስተካከያ ቅድሚያ ሰቶ ካላሻሻለ በስተቀር፤ ከዚህ ችግር መውጫ ዘዴ አይኖርም በማለት መንግስታት ከጦርነቱ በተያያዘ ለችግር የተጋለጡትን ዜጎች ወርደው በማየት መፍትሄ መፈለግ እንዳለባቸው ያሳስባሉ።

ብዙዎች የህብረቱ ዜጎች ግን ይህ አውዳሚ ጦርነት አሁን በአውሮፓ ከፈጠረው ችግር ይበልጥ በመጪው ግዚያት ሊያስክትል የሚችለው እንዳይብስ ነው ስጋታቸው።

 

ገበያው ንጉሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ 

አዜብ ታደሰ