1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርትአፍሪቃ

ጫማ ጠራጊ የኮሌጅ ተማሪዎች

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 16 2013

ጥበቢቱ ጥላሁን፣ ሰንበቶ በኔ እና ደሞዜ ዳንጊሶ በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ጎዳና ላይ ጫማ በማጽዳት ወይም በሊስትሮ ስራ ተሰማርተው ለእለት ኑሮና ለትምህርት ቤት ክፍያ የሚያሰፈልጋቸውን ወጪ በራሳቸው ይሸፍናሉ። 

https://p.dw.com/p/3n1KD
Äthiopien GirlZOffMute
ምስል S.Wegayehu/DW

የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ጫማ የሚጠረጉት ተማሪዎች

በኢትዮጵያ ከተማ ጎዳናዎች ላይ በርካታ  በሱሶች የተጠመዱ ታዳጊዎችን ማየት የተለመደ ነው። በአንጻሩ ደግሞ ከገጠር ወደ ከተማ መጥተው ባገኙት አነስተኛ ስራ ተሰማርተው፣ ራሳቸውን ሲረዱ የሚስተዋሉ ታዳጊዎች ቁጥርም የዛኑ ያህል ቀላል የሚባል አይደለም ። ለዚህም የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዶቻችን ጥበቢቱ ጥላሁን፣ ሰንበቶ በኔ እና ደሞዜ ዳንጊሶ ጥሩ ምሳሌ ሊሆኑ ይችላሉ። በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ የሚገኙት እነዚህ ወጣቶች ጎዳናዎች ላይ ጫማ በማጽዳት ወይም በሊስትሮ ስራ ተሰማርተው ለእለት ኑሮና ለትምህርት ቤት ክፍያ የሚያሰፈልጋቸውን ወጪ በራሳቸው ይሸፍናሉ። « የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች» #GirlZOffMute ዘጋቢ ወጣት ሊሻን ዳኜ  ወደ ስራ ቦታቸው ሄዳ አወያይታቸዋለች። 

ሊስትሮዋ የኮሌጅ ተማሪ


ሊሻን ዳኜ
ሸዋንግዛው ወጋየሁ / ልደት አበበ