1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዘንድሮው የፓሪስ ኦሎምፒክ የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ቅድመ ዝግጅት

ዓርብ፣ ሐምሌ 19 2016

ከሐምሌ 19 እስከ ነሐሴ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ባለው ጊዜ የሚከናወነው እና በ32 የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ከአስር ሺ በላይ አትሌቶች የሚሳተፉበት የዘንድሮው የፓሪስ ኦሎምፒክ የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ዛሬ በኢትዮጵያ ስዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ሁለት ስዓት አካባቢ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

https://p.dw.com/p/4inH2
የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ
የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ ምስል Thomas samson/AFP

የፓሪስ የኦሎምፒክ የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ቅድመ ዝግጅት ድባብ

 

ከሐምሌ 19 እስከ ነሐሴ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ባለው ጊዜ የሚከናወነው  እና በ32 የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ከአስር ሺ በላይ አትሌቶች የሚሳተፉበት የዘንድሮው የፓሪስ ኦሎምፒክ የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ዛሬ በኢትዮጵያ ስዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ሁለት ስዓት አካባቢ  ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።በፓሪስ ኦሎምፒክ የሚሳተፉ የኢትዮጵያ አትሌቶች በፈረንሳይ የሚለማመዱበት ቅድመ ሥምምነት ተፈረመ

በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ፣ በውኃ ዋና እና በቦክስ ስፖርቶች ትወከላለች።የብሬክ ዳንስ ውድድር ዘንድሮ በኦሊምፒክ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ይታያል ተብሏል።ለዘንድሮው ኦሎምፒክ 75 ሺህ ወታደሮችን ማሰማራቷ የሚነገርላት  ፓሪስ፤ በዛሬው ዕለት  33ኛውን የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የመክፈቻ ስነ ስረዓት ለመጀመር ጥቂት ሰዓታት በቀሩበት  የፈጣን ባቡር መስመር ላይ ጥቃት መፈፀሙ ተሰምቷል።በጥቃቱ የደረሰ ሰብአዊ ጉዳት ባይኖርም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የባቡር ተጓዦችን ጉዞ አስተጓጉሏል። 
የዘንድሮው  የፓሪስ ኦሎምፒክ ከአንድ ሰዓት ገደማ በኋላ  የመክፈቻ ስነስረዓት  በተለየ ሁኔታ የተወካይ ሀገራት ልዑካን ባሉበት ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።በመክፈቻ ስነስረዓቱ የማራቶን ከዋክብቶቹ  አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና አትሌት ትዕግስት አሰፋ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድንን በመምራት ይሳተፋሉ።  

 

 

ሙሉ ቃለምልልሱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ

 

ሐይማኖት ጥሩነህ

እሸቴ በቀለ 

ፀሀይ ጫኔ