«ለእርዳታ አቅርቦት የሚያስፈልግ ገንዘብ አጥሮኛል»የዓለም የምግብ ድርጅት
ሰኞ፣ ኅዳር 27 2014ማስታወቂያ
በመጪዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ለሚያስፈልገው የምግብ አቅርቦት ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት እንደገጠመው የአለም የምግብ ድርጅት አስታወቀ። የገንዘብ እጥረቱ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ለተጠለሉ የጎረቤት አገራት ስደተኞች የሚቀርበው የሰብዓዊ ድጋፍ ላይ እክል እንደሚፈጥር ድርጅቱ ገልጿል። በሰሜን ኢትዮጵያ ሦስት ክልሎች እንዲሁም በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች በግጭትና የተፈጥሮ አፎደጋዎች ምክንያት የተረጂዎች ቁጥር ማሻቀቡና የአለምአቀፍ ለጋሾች ድጋፍ አለመመጣጠን ለገንዘብ እጥረቱ ምክንያት መሆኑንም ድርጅቱ አስታውቋል።የዓለም የምግብ ድርጅት በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ለ12 ሚሊዮን ሰዎች የሕይወት አድን የምግብ እርዳታና የመተዳደሪያ ድጋፍ የሚያስፈልግ የ579 ሚሊዮን ዶላር እጥረት ገጥሞኛል ነው የሚለው።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ