1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወለጋ ተፈናቃዮች ሮሮ

ዓርብ፣ ጥቅምት 9 2016

2015 ዓ.ም. አምና ኪረሙ ምስራቅ ወለጋ ውስጥ በተከሰተው ደም አፋሳሽ ግጭት ተፈናቅለው አማራ ክልል ቻግኒ ከተማ ውስጥ ያሉ ተፈናቃዮች በእርዳታ እጦት እየተሰቃየን ነው አሉ፡፡ ቁጥራቸው 2400 እንደሆነ ለዶቼ ቬለ በሰጡት አስተያየት የገለጹት ተፈናቃዮቹ የተፈናቀሉትም አምና በህዳር 09 ቀን 2015 ዓ.ም የኪረሙ ግጭት ወቅት ነው ብለዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4Xnzu
Äthiopien I Binnenflüchtlinge in Gojjam
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የወለጋ ዞን ተፈናቃይ የአማራ ብሄር ተወላጆች ሮሮ እና የአካባቢ አስተዳደሮች ምላሽ

የወለጋ ተፈናቃዮች ሮሮ

2015 ዓ.ም. አምና ኪረሙ ምስራቅ ወለጋ ውስጥ በተከሰተው ደም አፋሳሽ ግጭት ተፈናቅለው አማራ ክልል ቻግኒ ከተማ ውስጥ ያሉ ተፈናቃዮች በእርዳታ እጦት እየተሰቃየን ነው አሉ፡፡

ቁጥራቸው 2400 እንደሆነ ለዶቼ ቬለ በሰጡት አስተያየት የገለጹት ተፈናቃዮቹ የተፈናቀሉትም አምና በህዳር 09 ቀን 2015 ዓ.ም የኪረሙ ግጭት ወቅት ነው ብለዋል፡፡ተፈናቃዮቹ መጠለያ እንኳ እንደሌላቸው ገልጸው በቤተክርስቲያን እና መስጊድ እንዲሁም ዘመድ ያለው ዘመዱ ጋር ተጠልሎ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡የምስራቅ ወለጋ ባለስልጣናት በፊናቸው ተፈናቃዮቹን ወደ ቀዬያቸው ለመመለስ በሁለቱ ክልሎች መካከል ውይይት እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡

ከተፈናቃዮች አንደኛው በሰጡን አስተያየት፤ “እስካሁን በመንግስት በኩል የደረሰን ድጋፍ የለም” ብለዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ በተለያዩ አከባቢዎች አሁን ባለው የጸጥታ ችግር የተነሳ ቀን ስራ እንኳ ሰርተው ቤተሰባቸውን ማስተዳደር ፈተና መሆኑን ያነሳሉ፡፡ በመንግስት በኩል እርዳታ ተልኳል እየተባለም ተፈናቃዮቹ ጋር የሚደርሰው እጅጉን ውስን በመሆኑ መንግስት የሰላ ክትትል ያድርግ ሲሉም ተፈናቃዮቹ ጠይቀዋል፡፡

ከወለጋ ተፈናቅለው ጎጃም ውስጥ የሚገኙ የአማራ ብሔር ተወላጆች
ከተፈናቃዮቹ የሚበዙቱ ህጻናት፣ ሴቶች እና አዛውንቶች ናቸውም ተብላል፡፡ ተፈናቃዮቹ በተለያዩ ቦታዎች ተበታትነው እንጂ የሚጠለሉበት ጣቢያ እንኳ አለመኖሩንም ያስረዳሉ፡፡ በአምናው ህዳር 09 የኪረሙ ግጭት በርካታ ሰው የሞቱበትና ድንገተኛ አወጣጥ በመውጣታቸው ይዘው የወጡት ንብረት አለመኖሩም ለከፋ ችግር እንደዳረጋቸው ይገልጻሉ፡፡ምስል Alemnew Mekonnen/DW

ከተፈናቃዮቹ የሚበዙቱ ህጻናት፣ ሴቶች እና አዛውንቶች ናቸውም ተብላል፡፡ ተፈናቃዮቹ በተለያዩ ቦታዎች ተበታትነው እንጂ የሚጠለሉበት ጣቢያ እንኳ አለመኖሩንም ያስረዳሉ፡፡ በአምናው ህዳር 09 የኪረሙ ግጭት በርካታ ሰው የሞቱበትና ድንገተኛ አወጣጥ በመውጣታቸው ይዘው የወጡት ንብረት አለመኖሩም ለከፋ ችግር እንደዳረጋቸው ይገልጻሉ፡፡ “ከቤተሰብ 21 ሰው ገደማ በእለቱ ተረሽኖብናል፡፡ የለበስናትን ልብስ ብቻ ነው ይዘን የወጣነው” ሲሉም ያላቸው ሁሉ በግጭቱ መውደሙን አስገንዝበዋልም፡፡ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው ጃራ አካባቢ የተጠለሉ ወገኖች አቤቱታ

ለ50 ዓመታት ገደማ ያፈራሁት ንብረት ነው በአንድ ጀንበር የወደመብን ያሉ ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ተፈናቃይም የከፋ ላሉት ችግር መዳረጋቸውን አስረድተዋል፡፡ “ለ50  ዓመታት ከኖርንበት ቀዬ ነው የተሰደድን፡፡ አገራችን እዚያው ነው ሌላ አገር የለንም፡፡ ያለንን ትለን ተሰደን መትተን የምንሰራ የለን አቅምም የለም፡፡ ገዝተንም ለመብላት ገንዘብ የለን፡፡ መድረሳም የለን ተንገላተናል፡፡”

ሌሎች አስተያየት ሰጪ ተፈናቃዮችም ሃሳበባቸውን ቀጠሉ፡፡ ተፈናቃዮች በነጻ ህክምና የሚገኙበት መንግድ እንኳ ባለመኖሩ ሊታከም በሚችል በሽታ እያለፉ ነው ብለዋል፡፡ በብዛት በአከባቢው ነዋሪ የእለት ጉርስ እንደሚያገኙ የገለጹት ተፈናቃዮቹ ያ ካተሳከ ጾማቸውን እንደሚውሉም አስረድተውናል፡የአማራ ክልል ተፈናቃዮች አቤቱታ፡ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ መስራትም ባለው የጸጥታ ሁኔታ ፈተና ነው ይላሉ ተፈናቃዮቹ፡፡በግጭቱ ባለቤታቸው ተገድለውባቸው ያላቸውን ሁሉ ጥለው ስድስት ልጆቻቸውን ይዘው መፈናቀላቸውን የሚገልጹት እናት ደግሞ ልጆቻቸውን ይዘው በረንዳ ብወድቁም የማበላቸው ፈተና ሆኖብኛል ሲሉ የተጋረጠባቸውን ፈተና ያስረዳሉ፡፡ማንም ቀርቦ ያወያየን የለም ሲሉ ምሬታቸውን የሚገልጹት ተፈናቃቹ ሰላም ወርዶ ወደ ቀዬያቸው መመለስ ግን ዋነኛው ፍላጎታቸው መሆኑን ያስረዳሉም፡፡ “መንግስት በመኪና አሳፍሮ ወደ ቀዬያችን ብመልሰን ደስታችን ነው”ብለዋል አንዱ ተፈናቃይ በአስተያየታቸው፡፡

ከወለጋ ተፈናቅለው ጎጃም የሚገኙ እናት እና ልጅ
ተፈናቃዮች በነጻ ህክምና የሚገኙበት መንግድ እንኳ ባለመኖሩ ሊታከም በሚችል በሽታ እያለፉ ነው ብለዋል፡፡ በብዛት በአከባቢው ነዋሪ የእለት ጉርስ እንደሚያገኙ የገለጹት ተፈናቃዮቹ ያ ካተሳከ ጾማቸውን እንደሚውሉም ተናግረዋል።ምስል Alemnew Mekonnen/DW

በምዕራብ ኦሮሚያ በተለይም በምስራቅ ወለጋ የተረጋጋ አንጻራዊ የሰላም ይዞታ መኖሩን የሚያስረዱት የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ገመዳ ተፈራ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ እንደሰጡት፤ አሁን ወደ ተለያዩ አከባቢዎች የተፈናቀሉ ተፈናቃዮችን መልሶ የማቋቋም ስራ ተጀምሯል ብለዋል፡፡ ኃላፊው እንዳሉት ከኦሮሚያ ክልል ውጪ የተፈናቀሉትንም ወደ ቀዬያቸው ወደ መመለስ ስራ ለመግባት በተለይም ከአጎራባች አማራ ክልል  አመራሮች ጋር ውይይት እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡ ተፈናቃዮችን ከመልሶ ማቋቋም ጎን ለበጎን ለመልሶ ማቋቋም የሚውሉ ተለያዩ መጠለያዎችን ከማዘጋጀት ጀምሮ እርዳታዎችን የማቅረብ ስራም መከወን እንዳለበት ታምኖ እየተሰራበት ይገኛልም ተብሏል፡፡

ሥዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ