1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮቪድ - 19 አስገዳጅ የመከላከያ ርምጃዎች

ሰኞ፣ መጋቢት 20 2013

የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ስርጭት አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል ያለው የጤና ሚኒስቴር ከዛሬ ጀምሮ በመከላከያ ዘዴዎቹ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ አሳስቧል።

https://p.dw.com/p/3rL7b
Äthiopien Addis Ababa | Maßnahmen gegen die Ausbreitung des Coronavirus
ምስል Solomon Muche/DW

የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ስርጭት በኢትዮጵያ አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል ያለው የጤና ሚኒስቴር ከዛሬ ጀምሮ በመከላከያ ዘዴዎቹ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ አሳስቧል። ማንኛውም ሰው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲጠቀም፣ ተቋማትም ይህንን ላላደረጉት አገልግሎት እንዳይሰጡ ፣ በቂ ርቀት እንዲጠበቅ እንዲሁም በማንኛውም ስብሰባ ላይ የግድ ካልሆነ በስተቀር ከ 50 በላይ ሰው እንዳይገኝ የሚያስገድደው መመሪያ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።  ከዛሬ ጀምሮ በጥብቅ ተግባራዊ እንዲደረግ የተላለፈው መመሪያ ከወራት በፊት የተደነገገ ነው። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰለሞን ሙጬ በከተማዋ ዞር ዞር ብሎ የመመሪያውን ተግባራዊነት ታዝቧል። 
ሰለሞን ሙጬ
ልደት አበበ
ሸዋዬ ለገሠ