1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮሮና ሥርጭት በአውሮጳ ያሳደረው ተጽዕኖ

ሐሙስ፣ የካቲት 26 2012

 በቻይና ኮሮና የገደላቸው ቁጥር ከ3ሺህ በልጧል።በቻይና በ24 ሰዓታት ውስጥ 31 ሰዎች ናቸው የሞቱት።በአውሮጳም ኮሮና መስፋፋቱና ሰዎችን መግደሉ ቀጥሏል። በኮሮና በተያዙ ሰዎች ብዛት ከአውሮፓ ቀዳሚውን ስፍራ በምትይዘው በኢጣልያ እስካሁን 79 ሰዎች ሞተዋል።በኢጣልያ በኮሮና የተያዙት ሰዎች ቁጥር ከ2500 በልጧል።በጀርመን ደግሞ 349 ደርሷል።

https://p.dw.com/p/3Yvci
Italien Mailand Coronavirus
ምስል picture-alliance/abaca/IPA

የኮሮና ተህዋሲ ዛሬም የስርጭት አድማሱን እያሰፋ ነው። በአሁኑ ጊዜ ኮሮና ከ70 በላይ በሆኑ ሃገራት ተሰራጭቷል።ተህዋሲው በተገኘባቸው ሃገራት በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም ከቀን ወደ ቀን መጨመሩ ቀጥሏል።በተህዋሲው የሚሞቱትም እንዲሁ። የኮሮና  ምንጭ በሆነችው  በቻይና ኮሮና የገደላቸው ቁጥር ከ3ሺህ በልጧል።ይህ አሃዝ በ24 ሰዓታት ውስጥ በቻይና የሞቱትን 31 ሰዎች ይጨምራል።በአውሮጳም ኮሮና መስፋፋቱና ሰዎችን መግደሉ ቀጥሏል። በኮሮና በተያዙ ሰዎች ብዛት ከአውሮፓ ቀዳሚውን ስፍራ በምትይዘው በኢጣልያ እስካሁን 79 ሰዎች ሞተዋል።በኢጣልያ በኮሮና የተያዙት ሰዎች ቁጥር ከ2500 በልጧል።በጀርመን ደግሞ 349 ደርሷል።ገበያው ንጉሴ ከብራሰልስ የኮሮና ሥርጭት በአውሮጳ ያሳደረውን ተጽእኖ ያስቃኘናል
ገበያው ንጉሴ 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ   
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ