1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋዮቹ የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ዞን ተቀጣሪዎች ቅሬታ፤

ዓርብ፣ ጥር 9 2017

በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ልማት ፖርክ ዉስጥ በተለያዮ ፋብሪካዎች ተቀጥረዉ የሚሰሩ ሠራተኞች የሚከፈለን ወርሀዊ ደመወዝ ከኑሮ ዉድነቱ ጋር የማይጣጣም አይደለም አሉ ።

https://p.dw.com/p/4pIa1
የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ
የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፎቶ ከማኅደር ምስል picture-alliance/dpa

የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ዞን ተቀጣሪዎች ቅሬታ፤

ኢንጂነር ዮናስ ብርሃኑ በኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኮምቦልቻ ኢንደስትሪ ፓርክ ካሉ ፋብሪካዎች በአንዱ ተቀጥሮ ይሠራል። የሚከፈለዉ ደመወዝና ኑሮ ግን አልጣጣም ብሎኛል ይላል።

ዓይንአዲስ ሞገስም ከቤተሰቦቿ ርቃ በኮምቦልቻ ኢንደስትሪ ፓርክ በሚገኝ ፍብሪካ መሥራት ከጀመረች አመታት እንደተቆጠሩ ትናገራለች። ጥረቴና ሥራየ ታይቶም በቅርቡ ደመወዝ ቢጨመርልኝም የግል ንፅሕና መጠበቂያ እንኳን ለመግዛት ተቸግሪያለሁ ትላለች።

ነኢማ እንድሪስ በፓርኩ ለሥራ ከተሠማሩት መካከል አንዷነች። በዓመት የሥራ ጥረት ውስጥ የሚገኘው ክፍያ ለእኛም በአግባቡ የሚበቃ ባለመሆኑ ቤተሰቦቻችንን ምን ይዘን እንጠይቅ በሚል ወደ እነርሱ ለመሄድ እንቸገራለን በማለት ትናገራለች።

በኮምቦልቻ ኢንደስትሪ ዞን ውስጥ ያሉ ሠራተኞች ከ1,700 ብር ጀምሮ መነሻ ደሞዝ የሚቀጠሩ ናቸው። በዚህም ምግብ በአግባቡ ለመብላት ይቸገራሉ ይላሉ የሠራተኞቹ ተወካዮች።

በኮምቦልቻ ኢንደስትሪ ዞን ባሉ ሠራተኞች የሚነሳዉ የደመወዝ ማነስ ጥያቄእንደ ሀገር የሚታይ ችግር ቢሆንም ችግሩን ለመፍታት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ሥራ እየሠሩ ነው የሚሉት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኮምቦልቻ ኢንደስትሪ ዞን ሥራ አስኪያጂ አቶ ሙሉጌታ መኮንን ናቸዉ

«እንደሀገርም የሚነሱ ጥያቄዎች ናቸዉ የኮምቦልቻ ችግር ብቻ አይደለም። ሁሉም አካባቢ ችግሮቹ ይነሳሉ። እንደማሳያ ጥያቄው የተነሳው እዚህ ሆኖ ካልሆነ በስተቀር ከዚህ በፊት ሥራና ከህሎት ሚንስቴር፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንና ሌሎቹም ችግሩን ለመቅረፍ  እየሠሩ ነው።» ብለዋል።

ኢሳያስ ገላው 

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ