1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የክልሎች ምክክር ምዕራፍ ሊጀመር ነው መባሉ

ሰኞ፣ ግንቦት 19 2016

ግጭት ውስጥ ያሉ አካላትን የማደራደር ሥልጣን በግልጽ የተሰጠን አይደለም ፤ ሆኖም በኛ ጥረት ግጭቶች ቢረግቡ ፣ ወደ ውይይቱ ቢመጡ የተቻለንን ያህል ጥረት እናደርጋለን"ብለዋል የስራ ሃላፊዎቹ። ታጣቂ ቡድኖች "አጀንዳችን ይሄ ነው ብለው በግልጽ" እንዲናገሩ ተደጋግሞ ጥሪ ቀርባል፤ሆኖም ከታጣቂዎች ምላሽ እንዳላገኙ ፍንጭ ሰጥተዋል።

https://p.dw.com/p/4gLNa
Äthiopien Addis Abeba | Büro der äthiopischen Kommission für den nationalen Dialog
ምስል Solomon Muchie/DW

የክልሎች ምክክር ምዕራፍ ሊጀመር ነው መባሉ

የክልሎች ምክክር ምዕራፍ ሊጀመር ነው መባሉ

ኢትዮጵያ ውስጥ በልሂቃን መካከል በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት አለመኖሩ፣ በመካከላቸው ያለው አለመተማመን እና ጥርጣሬ የዴሞክራሲ የሽግግር ሂደቱን ፈታኝ አድርጓል በሚል አስፈላጊነቱ ታምኖበት ታኅሣሥ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ማቋቋሚያ ዐዋጁ ጸድቆ፣ የካቲት 14 ቀን 2014 ዓ.ም 11 ኮሚሽነሮች ተሰይመለት ሥራ የጀመረው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ የክልሎች ምክክር ምዕራፍን ከፊታችን ረቡዕ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በአዲስ አበባ እንደሚጀምር ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረሥላሴ ዛሬ ተናግረዋል።

"በዚህ እርከን ላይ የሚመጡ ተሳታፊዎች በምክክር እና በውይይት የአጀንዳ ሃሳቦችን ያመጣሉ"ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለታጣቂዎች ያቀረበው የሰላም ጥሪ ምን ላይ ደረሰ?

ኮሚሽኑ ተሳታፊዎች በሚያፈልቁት ሀሳብ ይሁን በሚሰጡት አስተያየት ምንም ዓይነት ችግር እንደማይገጥማቸው ዋስትና እንደሚሰጥም ኃላፊዋ ገልፀዋል።

 

ኮሚሽኑ ታጣቂዎችን እና መንግሥትን የማደራደር ሥልጣን የለውም

 

በክልሎች ነፍጥ አንስተው ከመንግሥት ጋር እየተዋጉ ያሉ ታጣቂ ቡድኖች በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ውስጥ "አጀንዳችን ይሄ ነው ብለው በግልጽ" እንዲናገሩ ተደጋግሞ ጥሪ ቀርባል። ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ ኮሚሽኑ በዚህ ረገድ አደረገ ያሉትን ጥረት ሲገልፁ."ታጣቂ አካላት ወይም ግጭት ውስጥ ያሉ አካላትን የማደራደር ሥልጣን በግልጽ የተሰጠን አይደለም ለእኛ። ግን በእኛ ጥረት ግጭቶች ቢረግቡ ፣ ወደ ውይይቱ ቢመጡ የተቻለንን ያህል ጥረት እናደርጋለን" ብለዋል። የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሳታፊዎች ልየታ በአዳማ

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአዲስ አበባ የምክክር ምዕራፍ ማስታወቂያ
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአዲስ አበባ የምክክር ምዕራፍ ማስታወቂያምስል Solomon Muchie/DW

ግጭት ውስጥ ላሉት አካላት ጥሪ መደረጉን የገለፁት ሌላኛው ኮሚሽነር ዶክተር አምባዬ ኡጋቶ ከታጣቂዎች ምላሽ እንዳላገኙ ፍንጭ ሰጥተዋል።

 

ዋናው የምክክር ጉባኤ መቼ ይካሄድ ይሆን?

 

ምክትል ኮሚሽነር ሂሩት ገብረሥላሴ ስማቸውንና ቁጥራቸውን ባይገልፁም "በአሰራራችን እምነት እያገኙ የመጡ" ያሏቸው ፓርቲዎች አሉ። ዘጠኝ አባላት ያሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ኮከስ ግን አሁንም ከምክክሩ ሂደት ውጭ ነው።ሃገራዊ ምክክር በአሜሪካና ካናዳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር

የኮሚሽኑ የሥልጣን ጊዜ ከማብቃቱ በፊት ዋናውን የምክክር ጉባኤ ለመጥራት ጥረት እንደሚያደርጉም ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ ተናግረዋል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምስል Solomon Muchie/DW

 

የኢትዮጵያ ሁኔታና መፍትሔው 

እንዳስፈላጊነቱ በተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ጊዜው ሊራዘም እንደሚችል ተደንግጎ ሥራውን የኮሚሽነሮችን መሰየም ተከትሎ የካቲት 14 ቀን 2014 ዓ.ም የጀመረው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሥልጣን ዘመኑ 9 ወራት ይቀሩታል። በእርስ በርስ ጦርነት ፣ በትጥቅ ግጭት ፣ በሃይማኖትና በጎሳ ማንነት እና ፍላጎት ከሚስተዋለው ጭካኔ የተሞላበት መገዳደል እስከ እገታ እና  መንቀሳቀስ ያለመቻል ችግር የተወጠረችው ኢትዮጵያ ምን ብታደርግ ይበጃል? የሚለው ዐቢይ ጉዳይ አሁንም መፍትሔ የሚሻ ሆኖ ቀጥሏል።

ሰሎሞን ሙጬ

ኂሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ