1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የክልል ልዩ ኃይሎችን የማፍረሱ ስራ እና የገጠመው ተቃውሞ

እሑድ፣ ሚያዝያ 8 2015

የኢትዮጵያ መንግስት የክልል ልዩ ኃይሎችን በመበተን «በሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች ውስጥ መልሶ ለማዋቀር» ተግባራዊ የማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ በተለይ ከአማራ ክልል ሕዝባዊ ተቃውሞ ገጥሞታል። በክልሉ በበርካታ ከተሞች የታየው ተቃውሞው ገፍቶ የክልሉ ልዩ ኃይል እና የክልሉ ኢመደበኛ ታጣቂዎች ከመከላከያ ሰራዊት ጋር እስከመጋጨት ደርሰዋል

https://p.dw.com/p/4Q9TS
Äthiopien Tigray Soldaten Kämpfer
ምስል Eduardo Soteras/AFP/Getty Images

የክልል ልዩ ኃይሎች መፍረስ እና አንድምታው

የኢትዮጵያ መንግስት የክልል ልዩ ኃይሎችን በመበተን «በሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች ውስጥ መልሶ ለማዋቀር» ተግባራዊ የማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ በተለይ ከአማራ ክልል ሕዝባዊ ተቃውሞ ገጥሞታል። በክልሉ በበርካታ ከተሞች የታየው ተቃውሞው ገፍቶ  የክልሉ ልዩ ኃይል እና ሌሎች የክልሉ ኢመደበኛ ታጣቂዎች  ከመከላከያ ሰራዊት ጋር እስከመጋጨት ደርሰዋል፤ በግጭቱ ሰዎች ተገድለዋል፤ ቆስለዋል።

Äthiopien Konflikte
ምስል Eduardo Soteras/AFP/Getty Images

የክልል መንግስታት ልዩ ኃይሎቻቸውን የማደራጀት ስራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጠናከሩ መሄዳቸው ፤ በሂደትም ክልሎቹ ልዩ ኃይሎቻቸውን በትጥቅም ሆነ በቁጥር እያሳደጉ መሄዳቸው የሀገሪቱን የመከላከያ ሰራዊት እስከመገዳደር የደረሰ አቅም እንዲኖራቸው አስችሏል። ለዚህ ደግሞ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን ደም አፋሳሽ ጦርነት በማሳያነት መጥቀስ ይቻላል።

የክልል ልዩ ኃይሎች ከምስረታቸው ጀምሮ በአንድ በኩል ህገ መንግስታዊ መሰረት የሌላቸው እና የሀገሪቱን ደህንነት የሚያጋልጡ ናቸው በሚል ተቃውሞ ሲቀርብባቸው፤ በሌላ በኩል በየክልሉ የሚያጋጥሙ የፀጥታ ስጋቶችን በቅርበት ለመቆጣጠር እና የሕዝብን ደኅንነት ለማስጠበቅ  ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያበርክቱ ይችላሉ የሚል አስተያየት ሲሰጥበትም ይሰማል።  

Äthiopien Bahir Dar | Friedlicher Protest gegen Premierminister Abiy
ምስል Alemenew Mekonnen/DW

የሆነ ሆኖ የፌዴራሉ መንግስት የክልል ልዩ ኃይሎቹን «ትጥቅ ለማስፈታት ፣ ለመበተን እና መልሶ ለማዋሃድ » ከቅርብ ቀናት ወዲህ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ በተለይ ከአማራ ክልል ብርቱ ተቃውሞ ገጥሞታል። በተቃውሞው የክልሉን ልዩ ኃይል በተለየ ለማፍረስ ተፈልጓል የሚሉ አስተያየቶች ሲሰሙ በመንግስት በኩል ደግሞ ልዩ ኃይሎችን የማፍረስ እና የማዋሃዱ ስራ በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልጧል።

ልዩ ኃይሎቹን የማፍረስም ይሁን መልሶ የማዋሃድ ስራው አስፈላጊ ቢሆንም ካለው ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ጊዜውን ያልጠበቀ እና የህዝብን ደህንነት ለአደጋ ያጋለጠ ነው የሚል ትችትም ተደጋግሞ እየተሰማ ነው።

Äthiopien Soldaten der äthiopischen Nationalen Verteidigungskräfte (ENDF)
ምስል AMANUEL SILESHI/AFP/Getty Images

ልዩ ኃይሎችን የመበተን እና መልሶ የማደራጀት የመንግስት እርምጃ እና የገጠመው ብርቱ ተቃውሞ አንድምታ የዚህ ሳምንት የውይይት ርዕሳችን ነው።

ታምራት ዲንሳ