1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእርቀ ሰላሙ ሂደት መጓተት

ሐሙስ፣ ጥቅምት 12 2013

የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ብሔራዊ መግባባት እና አንድነት እንዲሁም እርቅ እንዲሰፍን ለማድረግ ባለፉት ጊዜያት የተከሰቱ ግጭቶችን እና ጉልህ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መሰረታዊ መንስኤዎችን እና ያስከተሉትን ተፅእኖዎች በመመርመር ተጎጂዎችንና በዳዮችን በማቀራረብ ዕርቅ የሚወርድበትን ሂደት ለመተለም ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/3kHu5
Äthiopien Versöhnungskommission in Addis Ababa
ምስል Solomon Muche/DW

«ሕዝቡን አለማወያየት የእርቀ ሰላሙን ሂደት አጓቷል።» የሰላም ኮሚሽን

ከዚህ በፊት የተከሰቱ እና ከተለያየ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሕዝብ ጥቆማ የቀረቡ ሀያ አንድ የግጭት ችግሮችን ለይቶ ደረጃ በደረጃ እያጠና እና ትንተና እየሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ዕርቀ ሠላም ኮሚሽን አስታወቀ።ኮሚሽኑ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 28 ቀን 2011 ዓ.ም በአዋጅ ከተቋቋመ ጀምሮ በኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል ሠላም፣ ፍትሕ፣ ብሔራዊ መግባባት እና አንድነት እንዲሁም ዕርቅ እንዲሰፍን ለማድረግ ባለፉት ጊዜያት የተከሰቱ ግጭቶችን እና ጉልህ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መሰረታዊ መንስኤዎችን እና ያስከተሉትን ተፅእኖዎች በመመርመር ተጎጂዎችንና በዳዮችን በማቀራረብ ዕርቅ የሚወርድበትን ሂደት ለመተለም ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።ይሁንና በፖለቲካ ተዋናዮች መካከል የፖለቲካ ስምምነት እና ከፍተኛ ያልተቋረጠ የሕዝብ ውይይት ባለመኖሩ ኮሚሽኑ ባሰበው ፍጥነት ሥራዎችን እንዳያከናውን እንቅፋት እንደሆነበት አስታውቋል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ