1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራ እና ሶማሊያ መሪዎች ጉብኝት

ዓርብ፣ ጥቅምት 30 2011

የኤርትራ እና የሶማሊያ ፕሬዝደንቶች ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ትስስር ለማጠናከር አማራ ክልል ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ  ጋር መምከራቸው ተሰምቷል። ፕሬዝደት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያው መሐመድ አብዱላሂ መሐመድ  ዛሬ ጎንደር ሲገቡ በአማራ ክልል ባለስልጣናት እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

https://p.dw.com/p/37y2x
Äthiopien President Somalia Mohammed Abdulahi, Eritreas Präsident Isayas Afeworki, Äthiopiens Premierminister Abiy Ahmed
ምስል Office of the Prime Minister-Ethiopia

ይፋዊው ጉብኝት ለሁለት ቀናት ይዘልቃል

 የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ለሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ያደርጋሉ። እስካሁንም በጎንደር የተለያዩ ታሪካዊ ቦታዎችንና የጎንደር ኒቨርሲቲን  ጎብኝተዋል፡፡  የምሥራቅ አፍሪቃ ሦስት ሃገራት መሪዎች ዝርዝሩ ይፋ ባይደረግም መስከረም ላይም ተገናኝተው መምከራቸው ይታወሳል። የሶማሊያው ፕሬዝደንት ታሪካዊ ነው ያሉት የሦስቱ ሃገራት ቅርርብ በአፍሪቃው ቀንድ ለውጥ የመምጣቱ ማሳያ ነው ማለታቸው ተሰምቷል። መሪዎቹ ወደ ባሕር ዳርም ዘልቀው በአካባቢው ጉዳዮች ላይ እየመከሩ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት በትዊተር ገፁ ያሰራጨው መረጃ ያስረዳል። በአቀባበል ሥነሥርኣቱ ላይ የባሕር ዳር ከተማን የሚወክሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የክልሉን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ተገኝተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣  ፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂና የሶማሊያው ፕሬዚደንት ሙሐመድ አብዱላሂ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ  በ207 ሚሊዮን ብር ያስገነባውን ሪፈራል ሆስፒታል ይመርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አለምነው መኮንን ከባሕር በቀጥታ ስልክ አነጋግረነዋል። 

አለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ተስፋለም ወልደየስ