1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 27 2016

በዘንድሮው የኢትዮጵያውያን የባህል ፌስቲቫል በአውሮፓ ያደጉ ወጣቶች እራሳቸውን እንደአንድ ቡድን አደራጅተው በእግርኳስ የተሳተፉበት እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል።

https://p.dw.com/p/4j57U
Belgien | Äthiopiens Sport and Cultural Festival in Brussels
ምስል Gebeyaw Nigusse/DW

ላለፉት ቀናት በበልጅየም ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያውያን የባህል ፌስቲቫል ዛሬ ተጠናቋል። መድረኩ ከስፖርትና የባሕል ትርኢቱ ባሻገር ኢትዮጵያውያንን የሚያቀረርብ እንደነበር ከበዓሉ አዘጋጆች ተገልጿል። በዘንድሮው የኢትዮጵያውያን የባህል ፌስቲቫል በአውሮፓ ያደጉ ወጣቶች እራሳቸውን እንደአንድ ቡድን አደራጅተው በእግርኳስ የተሳተፉበት እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል። የበልጅዩሙ ወኪላችን ገበያው ንጉሴ ስለዝግጅቱ አጭር ቃለምልልስ ሰጥቶናል የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያዳምጡት።

ገበያው ንጉሴ

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር