የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሰቆቃ በሳዑዲ አረቢያና የመን
ዓርብ፣ ሰኔ 19 2012ማስታወቂያ
በሳውድ አረብያና የመን እስር ቤቶችና ሌሎች ቦታዎች ያሉ ከ40 ሺህ በላይ የሚገመቱ ኢትዮጵያን ስደተኞች ሞትን ጨምሮ ለበሽታ እና ከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን አስታወቁ፡፡ በየእስር ቤቶቹ ታጉረው ካሉ ኢትዮጵያውያን መካከል 18 ስደተኞች መሞታቸው ተገልጿል፡፡ በኮረና ወረርሽኝ ስጋት የየመንና ሳውድ አረብያ ድንበር ከተዘጋ ወዲህ ወደ ሌላ ሀገር ለመሻገርም ሆነ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እንዳልቻሉ ስደተኞች ተናግረዋል። በተጠቀሱት ሃገራት ላለፉት 4 ወራት በእስራ እየተንገላታን ነው ያሉቱ ስደተኖቹ እስካሁን ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተደረገላቸው ጥረት እንደሌለም ገልጸዋል።
ሚሉዮን ኃይለስላሴ
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ