1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያዊያን ስፖርት እና ባሕል ፌዴሬሽን በአውሮፖ ፌስቲቫል

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 22 2015

በኔዘርላንድስ ዋና ከተማ አምስተርዳም ሲካሔድ የቆየው የኢትዮጵያዊያን ስፖርት እና ባሕል ፌዴሬሽን በአውሮፖ ፌስቲቫል ዛሬ ይጠናቀቃል። በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ የተመራ ልዑካን ቡድን ከአዲስ አበባ ወደ አምስተርዳም አቅንቶ ውይይት አድርጓል። ኢተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማን የመሳሰሉ እንግዶችም ተጋብዘዋል።

https://p.dw.com/p/4UXY3
Ethiopian sport and culture festival in Europe
የኢትዮጵያዊያን ስፖርት እና ባሕል ፌዴሬሽን በአውሮፖ ፌስቲቫልምስል Haimanot Tiruneh/DW

የኢትዮጵያዊያን ስፖርት እና ባሕል ፌዴሬሽን በአውሮፖ ፌስቲቫል

በኔዘርላንድስ ዋና ከተማ አምስተርዳም ሲካሔድ የቆየው የኢትዮጵያዊያን ስፖርት እና ባሕል ፌዴሬሽን በአውሮፖ ፌስቲቫል ዛሬ ይጠናቀቃል። ከተለያዩ የአውሮፓ አገራት ወደ አምስተርዳም የተጓዙ ኢትዮጵያውያን በፌስቲቫሉ ላይ ተሳትፈውበታል።

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ የተመራ ልዑካን ቡድን ከአዲስ አበባ ወደ አምስተርዳም አቅንቶ ውይይት ማድረጉን በቦታው የምትገኘው የዶይቼ ቬለዋ ሐይማኖት ጥሩነሕ ዘግባለች። ኢተርናሽናል ዳኛን በአምላክ ተሰማን የመሳሰሉ እንግዶችም ተጋብዘዋል። 

Ethiopian sport and culture festival in Europe
ምስል Haimanot Tiruneh/DW

በዚህ ፌስቲቫል ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ ቡድኖች በሁለት ዲቪዚዮን ተከፍለው የእግር ኳስ ጨዋታ አድርገዋል። የመጀመሪያው ዲቪዚዮን ዋንጫ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ከፍ ያለ አስተዋጽዖ ባበረከተው ሉቻኖ ቫሳሎ ስም ተሰይሟል። የሁለተኛው ዲቪዚዮን ዋንጫ ባለፈው ዓመት ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩት አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ፍቅሩ ኪዳኔ የተሰየመ ነው።

ከእግር ኳስ ጨዋታ በተጨማሪ ሥመ ጥር ኢትዮጵያውያን የተጋበዙበት የሙዚቃ ድግስ የመርሐ ግብሩ አካል ነበር። አብዱ ኪያር፣ ዳዊት መለሰ፣ ሸዋንዳኝ ኃይሉ እና ልጅ ሚካኤልን የመሳሰሉ ድምጻውያን ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ ሲካሔድ ለቆየው  የኢትዮጵያዊያን ስፖርት እና ባሕል ፌዴሬሽን በአውሮፖ ፌስቲቫል ከተጋበዙ መካከል ይገኙበታል። 

ሐይማኖት ጥሩነህ
እሸቴ በቀለ