1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የሰላም ጥሪ

ሐሙስ፣ ግንቦት 29 2016

ቅዱስ ሲኖዶስ፤ በሀገሪቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ ከቤተ ክርስትያን መሪዎች እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ የተባሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ እንደማይቀበላቸው እና በጥብቅ እንደሚቃወማቸው ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/4gkTi
ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረጉ ግጭቶች በሠላም እንዲፈቱ ቤተ ክርስቲያኒቱ ጠይቃለች
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያሪክ አቡነ ማቲያስ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡምስል DW/G. Tedla

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የሠላም ጥሪ

ኢትዮጵያውስጥ ብርቱ ሞት እና መፈናቀል እያደረሰ ያለውን አለመግባባትና ግጭት የሚመለከታቸው ሁሉ በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥሪ አደረገች። 

የቤተክርስትያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ያደረገውን ምልዓተ ጉባኤ ተከትሎ በወጣው መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ ከቤተ ክርስትያኗ መሪዎች እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ የተባሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ እንደማይቀበላቸው እና በጥብቅ እንደሚቃወማቸው ተገልጿል። 

ከሀገራዊምክክር ኮሚሽን እስካሁን የቀረበላት የተሳትፎ ጥሪ እንደሌለ ያስታወቀችው ቤተ ክርስትያኗ ሆኖም የተሳታፊ ልየታንና የአጀንዳ መረጣ ሥራ ተጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ መገባቱ ቅዱስ ሲኖዶስን ቅር እንዳሰኘ አስታውቃለች።// 

ግጭትእንዲወገድ የቀረበው ጥሪ 

የኢትዮጵያኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ በመግለጫቸው ሕይወት እየቀጠፈ፣ ውድመትም እያስከተለ ያለው ግጭት እንዲወገድ ጠይቀዋል። 

"በመላው ሀገራችንበተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንኦት ጥሪውን ያቀርባል"     

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን በየአካባቢዉ የሚደረገዉን ግጭት ለማስቆም ሁሉም ወገኖች እንዲወያዩ ጠይቃለ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን በየአካባቢዉ የሚደረገዉን ግጭት ለማስቆም ሁሉም ወገኖች እንዲወያዩ ጠይቃለችምስል Seyoum Getu/DW

የቤተክርስትያን ያልሆኑ መልእክቶች 

የሃይማኖትጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ተብሎ የታመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦችን በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክ ውሳኔ ያሳለፈው ቅዱስ ሲኖዶስ፤ በሀገሪቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ ከቤተ ክርስትያን መሪዎች እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ የተባሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ እንደማይቀበላቸው እና በጥብቅ እንደሚቃወማቸው ተገልጿል። 

የግብረሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ጉዳዮች 

ፓትርያርኩ ሌላው በመግለጫቸው ያነሱት በብዙ መስፈርት ተቀባይነት የሌለው የተባለውን የግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትንየተመለከተውን ገዳይ ነው። 

"ግብረ ሰዶማዊነትናየተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ የተከለከለ፣ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ እያወገዘ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና የግብረ ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል" ብለዋል። 

የሀገራዊምክክር ተሳትፎ  

የኢትዮጵያኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ሆና ሳለ እስከአሁን ድረስ በይፋ ከሀገራው ምክክር ኮሚሽን የተሳትፎ ጥሪ እንዳልቀረበላት በመግለጫው ተጠቅሷል። 

በዚህምቅዱስ ሲኖዶስን ቅር መሰኘቱ ተነግሯል። ቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ያለችውን ኮሚቴ መሰየማም ተገልጿል። 

ሶሎሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ