1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውይይት፦ የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር የሚያስከፍለው ዋጋ በማን ላይ ይበረታል?

Eshete Bekeleእሑድ፣ ሐምሌ 21 2016

የኢትዮጵያ መንግሥት ተግባራዊ የሚያደርገው የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር አካል የሆኑ የተለያዩ አዋጆች ባለፉት ወራት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቀዋል። ለመሆኑ የኤኮኖሚ ማሻሻያው የሚያስከፍለው ዋጋ በማን ጫንቃ ላይ ይወድቃል? በኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሚና ምንድነው? በዚህ ውይይት የገንዘብ አስተተዳደር ባለሙያው ዶክተር አብዱልመናን መሐመድ፣ በዓለም አቀፍ ተቋም ውስጥ ከፍተኛ ተመራማሪ ሆነው በመሥራት ላይ የሚገኙት ዶክተር ቀልቤሳ መገርሳ እና በዩናይትድ ኪንግደም ብሪስቶል ዩኒቨርሲቲ ሥር በሚገኘው ፔሪቮሊ አፍሪካ ጥናት ማዕከል ተመራማሪው ዶክተር ኢዮብ ባልቻ ተሳትፈዋል።

https://p.dw.com/p/4inGT
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ስለዚሕ ዝግጅት

ስለዚሕ ዝግጅት

Äthiopien Guba | Grand-Ethiopian-Renaissance-Talsperre
ምስል Amanuel Sileshi/AFP/Getty Imagesምስል Amanuel Sileshi/AFP/Getty Images

እንወያይ

በሣምንቱ በተከሰቱ የኢትዮጵያ ዐበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ዶይቼ ቬለ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን በመጋበዝ ውይይት ይካሔዳል። በውይይቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎች ይጋበዛሉ። ውይይቱ ዘወትር እሁድ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል።