1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች ኢትዮጵያ የተባለው ማህበር የዘፈቀደ እስር እንዲቆም ጠየቀ

ዓርብ፣ ሰኔ 14 2016

ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ የተባለ ሲቪክ ተቋም ሰሞኑን የተለቀቁ ሰዎችን በተመለከተ እርምጃውን በበጎ እንደሚመለከተው ገልፆ፣ አሁንም ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ አርቲስቶች እና ፖለቲከኞች በዘፈቀደ እንደታሰሩ መሆኑን፣ መንግሥት "እየፈጸመ ያለው የመሠረታዊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰትም ቀጥሏል" በማለት እንዲታረም ጠይቋል።

https://p.dw.com/p/4hLYE
ስብስብ  ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ የተባለ ሲቪክ ተቋም መሠረታዊ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንዲታረም ጠይቋል።
ስብስብ  ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ የተባለ ሲቪክ ተቋም መሠረታዊ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንዲታረም ጠይቋል።ምስል Felix Kästle/dpa/picture-alliance

በእስር ላይ የሚገኙ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እንዲፈቱ ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች ማህበር ጠየቀ

 

የዋስትና መብታቸው ያልተከበረላቸው ታሳሪዎች

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ የኢሕአፓ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራን ጨምሮ በገንዘብ ዋስትና ከእሥር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት የወሰነላቸው ዘጠኝ ሰዎች ጉዳያቸው ለመጭው ሰኞ ቀነ ቀጠሮ ተይዞለታል።የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በዋስትናው ላይ ፖሊስ  በጠየቀው ይግባኝ ብይን ለመስጠት ለዛሬ አርብ ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም፤ ፍርድ ቤቱ «መዝገቡን ስላላቀረቡልኝ መወሰን አልቻልኩም» በሚል ብይኑን ለሰኞ ቀጥሮ መስጠቱ ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ስብስብ  ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ የተባለ ሲቪክ ተቋም ሰሞኑን የተለቀቁ ሰዎችን በተመለከተ እርምጃውን በበጎ እንደሚመለከተው ገልፆ፣ አሁንም ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ አርቲስቶች እና ፖለቲከኞች በዘፈቀደ እየታሰሩ መሆኑን፣በመጥቀስ  ማህበሩ ቀጥሏል ያለውን መሠረታዊ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንዲታረም ጠይቋል።

ለኢሕአፓ ፕሬዝዳንትና ለሎችም የተበየነው የዋስትና መብት ዛሬም አልተፈፀመም

የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ግለሰቦቹ ሰኞ እለት በገንዘብ ዋስትና እንዲወጡ መወሰኑን ተከትሎ ለአምስቱ ተጠርጣሪዎች ሰላሳ ሺህ ብር፣ ለአራቱ ደግሞ የሃያ ሺህ ብር ዋስትና ፈቅዶ ነበር። ይሄው አፈፃፀም ከተከናወነ በኋላ ፖሊስ ይግባኝ በመጠየቁ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በዚሁ ላይ ብይን ለመስጠት ለዛሬ አርብ ቀጠሮ ይዞ ነበር።ኢሰመጉ የእስረኞችን አያያዝ ለማየት ፈቃድ ተከለከልኩ አለ

ሆኖም ፍርድ ቤቱ መዝገብ ጠፍቷል በሚል መዝገቡ ስላልቀረበለት መወሰን ባለመቻሉ ለሰኞ ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ. ም ቀጠሮ መስጠቱን የኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።

በእሥር ላይ የሚገኙት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ዋስትና 

በተመሳሳይ ማህበራዊ ጉዳዮችን የሚዳስሰው "እብደት በሕብረት" የተባለው የመድረክ ተውኔት ተዋናይ አመኑኤል ሀብታሙ ፣ አዘጋጁ ዳግማዊ ፈይሳ እና የሌሎችም ተጠርጣሪ ከያንያን የዋስትና መብታቸው ትናንት ሐሙስ ቢፈቀድም ዛሬም በእሥር ላይ መሆናቸውን ጠበቃቸው አረጋግጠዋል።

.ተዋናይ አማኑኤል ሀብታሙ ከእስር እንዲፈታ ፍርድ ቤቱ ቢወስንም እስካሁን አለመፈታቱን ጠበቃው ገልፀዋል።
በቅርቡ በቁጥጥር ስር የዋለው ተዋናይ አማኑኤል ሀብታሙ ከእስር እንዲፈታ ፍርድ ቤቱ ቢወስንም እስካሁን አለመፈታቱን ጠበቃው ገልፀዋል።ምስል privat

ህገ - መንግሥታዊ ሥርዓትን በትጥቅ ትግል ለመቀየር ተንቀሳቅሰዋል በሚል ተጠርጥረው ከተያዙ ግለሰቦች መካከል 17ቱ እያንዳንዳቸው በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ትናንት ሐሙስ ብይን ሰጥቶ ነበር። ጠበቃቸው አያሌው ቢታኔ ለዶቼ ቬለ እንዳሉት ደንበኞቻቸው ዛሬ አልተለቀቁም።

የመብት ድርጅቶች ውትወታ

ስለ ተፈፃምነቱ ማብቃትም ሆነ መራዘም ከመንግሥት እንዲህም ነው እንዲያም ነው ባይባልም፣ በአማራ ክልል ታውጆ ለአሥር ወራት የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተከትሎ ለወራት በእሥር ላይ የቆዩት ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ፣ ጋዜጠኞች በላይ ማናዬ፣ ቴዎድሮስ ዘርፉ እና በቃሉ አላምረው በቅርቡ ከእሥር መፈታታቸውን በበጎ እንደሚያየው ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ የተባለው ተቋም ገለጿጻ። ተቋሙ እንደሚለው አሁንም ጥቂት ያልሆኑ ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ አርቲስቶች እና ፖለቲከኞች በዘፈቀደ እንደታሰሩ ሲሆን፤ መንግስት እየፈፀመ ነው ያለው "የመሠረታዊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ቀጥሏል።" የሰብዓዊ መብት ሁኔታ በኢትዮጵያ

መንግስት የዜጎችን መሰረታዊ መብቶች ማለትም ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የፕሬስ እና ሌሎች መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብር እና እንዲያከብር የጠየቀው ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ፤ መንግሥት በጥርጣሬ ለታሰሩት ሁሉ ፍትሕ የማግኘት እና የመዳኘት መብታቸውን እንዲያከብር የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ መሰረት ዐሊ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እና መድረኮች ላይ "ወከባዎች፣ ክልከላዎች፣ እሥር እና ጫናዎች ከእለት እለት እየበረቱ መምጣታቸው" እንዳሳሰበው፣ የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከልም በትያትር እና ጥበብ መልኩ የሚቀርቡ ሥራዎችን የማገድ እንዲሁም የትያትር ባለሙያዎችን ለእሥር የመዳረግ እርምጃዎች በተደጋጋሚ እየተከሰቱ መሆኑን፣ ይህም እየሆነ ያለው ያለ አግባብ ከተለመደው ነገር ግን "ሕገ መንግሥታዊ ሀሳብን የመግለጽ ነፃነትን ከሚጋፋው የጋዜጠኞች የዘፈቀደ እሥር ጎን ለጎን ነው" ሲሉ አቤት ያሉት በቅርቡ ነበር።

ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

ሰለሞን ሙጨ

አዜብ ታደሰ

ፀሀይ ጫኔ