1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሲኖዶስ ዉግዘትና ዉሳኔ

ረቡዕ፣ የካቲት 11 2012

የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እናቋቁማለን በማለት የሚንቀሳቀሱ ባላቸው ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን ፣ አባ ገብረ ማርያም ነጋሳ፣ መምህር ኃይለሚካኤል ታደሰ እና ቄስ በዳሳ ቶላ ላይ ከዛሬ ጀምሮ ከቤተ ክርስትያን የተሰጣቸው ክህነት መያዙንና በቤተ ክርስትያኒቱ ስም ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ አግዷል።

https://p.dw.com/p/3Y0mL
Äthiopien Addis Abeba | Pressekonferenz der äthiopischen orthodoxen Kirche:  Patriarch Aab Mathias
ምስል DW/S. Muche

የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዉግዘት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባለፈ ጥር ማብቂያ በአዲስ አበባ ዉስጥ ሁለት ምዕመናን መገደላቸዉንና ሌሎች መጎዳታቸዉን አወገዘ።በሌላ በኩል ከቤተ ክርስትያኒቱ ህግና ደንብ ውጪ፣ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እናቋቁማለን በማለት የሚንቀሳቀሱ ባላቸው ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን ፣ አባ ገብረ ማርያም ነጋሳ፣ መምህር ኃይለሚካኤል ታደሰ እና ቄስ በዳሳ ቶላ ላይ ከዛሬ ጀምሮ ከቤተ ክርስትያን የተሰጣቸው ክህነት መያዙንና በቤተ ክርስትያኒቱ ስም ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ አግዷል።

ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ