Eshete Bekele/MMTረቡዕ፣ ሐምሌ 10 2016የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ማዕከላዊ ባንክ 817 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው የመገበያያ ገንዘብ ልውውጥ ሥምምነት ተፈራርመዋል። ባንኮቹ ሥምምነቱ “በሁለቱ ሀገራት መካከል የፋይናንስ እና የንግድ ትብብርን ይደግፋል” ብለዋል። ሥምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ማዕከላዊ ባንክ ገዥ ኻሊድ ሞሐመድ ባላማ ናቸው። ባንኮቹ በድንበር ተሻጋሪ ክፍያዎች ብር እና ድርሐም የበለጠ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማድረግ እንዲሁም የክፍያ እና የመልዕክት መለዋወጫ ሥርዓቶችን ለማስተሳሰር የመግባቢያ ሥምምነቶች ተፈራርመዋል።