1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ዘገባ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 11 2016

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን የ2016 በጀት ዓመት 227 የውጭ ሀገር ባለሀብቶችን ያካተተ በአጠቃላይ 329 አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን ዋና ኮሚሽነር ሃና አርአያ ሥላሴ አመለከቱ። ከአማራ፣ ከኦሮምያ እና ከድሬደዋ ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤቶች ጋር ለውጭ መዋዕለ ንዋይ ምቹ እና የተለየ ጥበቃ ለማመቻቸት መወያየታቸውንም ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/4iTpR
የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ
የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፎቶ ከማኅደርምስል AFP/E. Jiregna

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ዘገባ

 

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የ2016 በጀት ዓመት 227 የውጭ ሀገር ባለሀብቶችን ያካተተ በአጠቃላይ 329 አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን ዋና ኮሚሽነር ሃና አርአያ ሥላሴ አመለከቱ። ከክልል መንግሥታት በተለይ ከአማራ፣ ከኦሮምያ እና ከድሬደዋ ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤቶች ጋር ለውጭ መዋዕለ ንዋይ ምቹ እና የተለየ ጥበቃ ለማመቻቸት መወያየታቸውን የተናገሩት ኮምሽነሯ በጸጥታው ሂደት ጥሬ ዕቃ ማስገባት ሳይችሉ ቀርተው ከአቅማቸው በታች የሚሠሩ አንዳሉም ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

በያዝነው የበጀት ዓመት 329 አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን እና ከነዚህም ውስጥ 46ቱ የሀገር ውስጥ እንዲሁም 62ቱ በሽርክና የመጡባለሃብቶች መሆናቸውን ገልፀው በግጭት ምክንያት ከ ሰሜኑ የሀገሪቱ ክልል የውጡትን ኢንቨስተሮች ዳግመኛ ለመጥራት ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ስምምነት መድረሳቸውን ተናግረዋል።

2016 በጀት ዓመት 3.82 ቢሊየን ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በማስመዝገብ ከዕቅዱ 80 በመቶ አሳክቻለሁ ያለው የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ11.5 በመቶ ዕድገት አሳይቷ ነው ያሉት ኮምሽነር።

በዚህ ዓመት አዲስ ፈቃድ ከወሰዱ ባለሀብቶች መካከል ምን ያህሉ በርግጠኝነት ገብተው ሥራ እንደ ጀመሩ በዘገባው ላይ ያስቀመጠው ነገር ባይኖርም ቻይና፣ ህንድ እና ጂብቲ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ ፍሰት ያደረጉ ሃገራት መሆነቸው ተነግሯል። 

በሌላ በኩል ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የውጭ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሽ ለዶቼቪሌ እንደተናገሩት በርግጥ የውጭ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ፍላጎቱ እና ተነሳሽነቱ ቢኖርም ሕጋዊ የሆነ የአሠራር ሰነድ እስካሁን ባለመኖሩ አስቸጋሪ ሁኔታን ፈጥሯል ይላሉ ።

ሃና ደምሴ

ሸዋዬ ለገሠ

ታምራት ዲንሳ