1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ቴክኒክአፍሪቃ

የኢትዮ ቴሌኮም አዲስ የግንኙነት ማዕከል

ረቡዕ፣ ጥቅምት 9 2015

ኢትዮ ቴሌኮም በተለያዩ አማራጮች አገልግሎት ይሰጣል ያለውን አዲስ የግንኙነት ማዕከል ይፋ አደረገ። ይኽ አዲስ የግንኙነት ማዕከል የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚ ተቋማት ወይም ድርጅቶች ማሰራጨት የሚፈልጉትን መረጃ ከየትኛውም ቦታ በፈለጉት አይነት የማኅበራዊ ትስስር ገፅ አማራጭ ለደንበኞቻቸው በአንድ ጊዜ ተደራሽ የሚያደርጉበት ነው ተብሏል።

https://p.dw.com/p/4IQYV
Äthiopien Reportage aus Mekelle
ምስል Million Hailessilassie/DW

ኢትዮ ቴሌኮም

የኢትዮጵያ ቴሌኮም ከደንበኞች የግኙነት አገልግሎት ባሻገር የዲጂታል አገልግሎትን በማቅረብ በሀገር ውስጥ ያሉ ድርጅቶች በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ብልሀት ተጠቅመው ሥራቸውን የተቀላጠፈ ብሎም የበለጠ ተደራሽ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የግንኙነት ማእከል ኮንታክት ሴንተር  መጀመሩን ስታውቋል። ይህ በተለያዩ አማራጮች አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አዲስ የግንኙነት ማዕከል ወይም ኮንታክት ሴንተር የኢትዮ ቲሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚ ተቋማት ወይም ድርጅቶች ማሰራጨት የሚፈልጉትን መረጃ ከየትኛውም ቦታ በፈለጉት አይነት የማኅበራዊ ትስስር ገፅ አማራጭ ለደንበኞቻቸው በአንድ ጊዜ ተደራሽ የሚያደርጉበት ነው ተብሏል። ይህም ተገልጋዮች መደበኛ የስልክ ኔትዎርክን ጨምሮ ሁሉንም የማኅበራዊ መገናኛ አማራጮች ሁሉ በመጠቀም የሚፈልጉትን አገልግሎት በቀላሉ የሚያገኙበት ነው። የተለያዩ የመገናኛ ስልቶችን ወደ አንድ መድረክ በማምጣት ለደንበኞች ቀጥተኛ አገልግሎት አማራጭ፤ ለተቋማት እና ለድርጅቶች መስጠት መጀመሩ የኢትዮ ቲሌኮምን ወጪ እንደሚቀንስ ነው የተነገረው። በሌላ በኩል በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የስልክ አገልግሎት ያለመኖር እንዲሁም በጥራት ችግር እንደልብ  ተደራሽ  እንዳልሆነም ይነገራል። በተለይ  ከከተማ ወጣ ባሉ አካባቢዎች ደግሞ ችግሩ ይሰፋል።  «ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ» በአዲስ አበባ ስራ ጀመረብዙዎች ከኢትዮ ቲሌኮም በተጨማሪ ሳፋሪ ኮም የተሰኘው የስልክ አገልግሎት ሰጭ በሀገራችን መግባቱ የሚታየውን የአገልግሎት ተደራሽነት ችግር ሊቀርፍ በዚያም ላይ በዋጋ እና በአገልግሎት በኩልም የተሻለ አማራጭ እንዲኖረው ያስችላል የሚል ተስፋ አላቸው። ድርጅታቸው የቴሌኮም ተደራሽነት እና ጥራት ቁጥጥር ላይ እንደሚሠራ የሚናገሩት የኢትዮጵያ ኮምንኬሽን ባለሥልጣን የተደራሽነት እና ሁሉን አቀፍ ዳይሪክቶሪት ዳይሪክተር አቶ አሰግደው ፍሰሀ አወቅ፤ በተለያዩ አካባቢዎች የጥራት እና ተደራሽነት ላይ የሚነሱ ጥያቂዎች መኖራቸውን ያረጋግጣሉ።

Firehiwot Tamiru
የኢትዮ ቴሌኮም ሥራ አስኪያጅ ፍሬሕይወት ታምሩ ምስል Hanna Demissie/DW
Äthiopien Telecom 5G Internet Service
ኢትዮ ቴሌኮም 5Gን ይፋ አድርጓልምስል Solomon Muchiee/DW

የኢትዮ ቲሌኮም በኢትዮጵያ ከፍተኛ የኔት ወርክ ሽፋን አለው 98 ከመቶ የሚሆን ህዝብ ዘንድ ተደራሽ ነው። ከዚህ ውጭ ያሉ አንዳድን ቦታዎች ላይ ያለውን የተደራሽነት ችግር ተቋማቸው ጥናት አድርጎ መረጃውን እንደያዘና በዚህ መሰረት ችግሩን ለማስወገድ እንደሚሠራም አቶ አሰግድ ተናግረዋል። የጥራት እና የተደራሽነት ችግር ከከተማ ውጭ ሳይሆን ከተማ ውስጥም በየጊዜው የሚገጥም ነገር ነው ያሉት ባለሙያው « የቴሌኮም አገልግሎት መሰረተ ልማት ግንባታ በጣም ውጭ ይጠይቃል ለዚህም  የቴሌኮም ኩባንያዎች ፍላጎት እና ገበያ ያለበትን አካካባቢ ለመምረጥ ይገደዳሉ» ብለዋል።

ሃና ደምሴ 

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ