1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሰላም ስምምነቱ ላይ የሁለቱ የአገው የፖለቲካ ድርጅቶች እሰጣ ገባ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 26 2016

“የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አዴን) ከአማራ ብሔራዊ ክልል ጋር ሰሞኑን ያደረገው የሰላም ስምምነት የአገው ህዝቦችን ፍላጎት አያሟላም” ሲል የአገው ብሔራዊ ሸንጎ ያወጣውን መግለጫ የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አዴን) እንደማይቀበለው አስታወቀ። ስምምነቱ ሁሉንም የአገው ፓርቲዎች ማካተት ነበረበት ሲል ሸንጎው ስምምነቱን ውድቅ አድርጎታል፡፡

https://p.dw.com/p/4au4i
የአገዉ ሕዝብን እንወክላለን የሚሉ ሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተወዛገቡ ነዉ
የአገዉ ሕዝብ ከሚታወቅበት ባሕሉ አንዱ የፈረስ ግልቢያ ፉክክር ነዉምስል Alemnew Mekonnen/DW

የአገው ብሔራዊ ሸንጎ እንደማይቀበል አገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አስታወቀ

በሰላም ስምምነቱ ዙሪያ የሁለቱ አገው የፖለቲካ ድርጅቶች እሰጣ ገባ

 “የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አዴን) ከአማራ ብሔራዊ ክልል ጋር ሰሞኑን ያደረገው የሰላም ስምምነት የአገው ህዝቦችን ፍላጎት አያሟላም” ሲል የአገው ብሔራዊ ሸንጎ ያወጣውን መግለጫ የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አዴን) እንደማይቀበለው አስታወቀ። ስምምነቱ ሁሉንም የአገው ፖለቲካ ፓርቲዎች ማካተት ነበረበት ሲል ሸንጎው ስምምነቱን ውድቅ አድርጎታል፡፡

የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አዴን) ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከአማራ ክልላዊ መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት አድርጓል ይህን አስመልክቶም ስምምነቱን አስመልክቶ ለአካባቢው ነዋሪዎች በሰቆጣ ከተማ ታህሳስ 21 /2016 ይፋ አድርጓል፡፡

የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አስመልክቶ የአገው ብሔራዊ ሸንጎሊቀመንበር አቶ አላምረው ይርዳው ዛሬ ለዶይቼ ቬሌ በሰጠው አስተያየት አዴን ከክልሉ መንግስት ጋር ያደረገው የሰላም ስምምነት የንቅናቄውን አባላት የማይወክል፣ በጫናና በግለሰቦች ፍላጎት የተደረገ በመሆኑ ሰምምነቱ ለአገው ህዝብ ጥያቄ መልስ የማይሰጥና ተቀባይነት የለውም ሲል ውድቅ አድርጎታል፡፡የአገው ብሔራዊ ሸንጎ ተቃዉሞ

“ለነርሱም፣ ለአገው ህዝብም ክብር አይመጥንም፣ በአጠቃላይ ስምምነቱ ከአደራዳሪው አንፃር፣ ሸንጎንና ሌሎች ፓርቲዎችን ካለማካተት አንፃር፣ መስፈርት የሌለው ስምምነት ነው፡፡ስምምነቱ ራሱ አንዲት ቅንጣት ለአገው ህዝብ የሚጠቅም ነገር የለውም፡፡”

የአገው ብሄራዊ ንቅናቄ ጋዜጣዊ መግለጫ
የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አስመልክቶ የአገው ብሔራዊ ሸንጎሊቀመንበር አቶ አላምረው ይርዳው ዛሬ ለዶይቼ ቬሌ በሰጠው አስተያየት አዴን ከክልሉ መንግስት ጋር ያደረገው የሰላም ስምምነት የንቅናቄውን አባላት የማይወክል፣ በጫናና በግለሰቦች ፍላጎት የተደረገ በመሆኑ ሰምምነቱ ለአገው ህዝብ ጥያቄ መልስ የማይሰጥና ተቀባይነት የለውም ሲል ውድቅ አድርጎታል፡፡ምስል Seyoum Getu/DW

እንደ አቶ አላምረው ለአገውን ህዝብ ሰላም፣ እድገትና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር የሚታገሉ ፓርቲዎች በሙሉ በሰላም ስምምነቱ መሳተፍና ዘላቂ ሰላም ማምጣት ነበረባቸው፡፡

“ይህ ጉዳይ የአገው ብሔራዊ ሸንጎን በደንብ ይመለከታል፣ እንኳን የተደራጀውን አገው ቀርቶ ልተደራጀውን አገው ይመለከታል፣ ብዙ የአገው ልጆች በትግሉ ተሰውተዋል በመሆኑም ሁሉም ለአገው ህዝብ የቆሙ ኃይሎች ካልሆነም ደግሞ የአገው ብሔራዊ ሸንጎ በሰላም ውይይቱ መሳተፍ ነበረባቸው፡፡”

የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አዴን) ሊቀመንበር አቶ ኪሮስ ሮምሀ በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ እንዳሉትየአገው ብሔራዊ ሸንጎ ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ የሰጠው መግለጫ ተገቢነት የሌለውና በሌላ ፓርቲ ጣልቃ መግባት ነው ወንጀልም ነው ብለዋል፣ የሰላም ስምምነቱም የግለሰቦች ሳይሆን የንቅናቄውማዕካለዊ ኮሚቴ ያመነበትና የተወያየበት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ከአማራ ክልል የሰላም ሥምምነት የተፈራረመው የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አመራሮች ሹመት እንደሚሰጣቸው ሊቀ-መንበሩ ተናገሩ

“የግለሰቦች ነው ይላል፣ይህ አግባብነት የሌለው ስምታ ነው፣ 19 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አሉን፣ አንድ ብቻ ነው ሂደቱንየተቃወመው፣ 18ቱ ተስማምተው ስምምነቱን ተቀብለዋል፣ ህዝባችን እያማከርን፣ ሥራ አስፈፃሚ እያየው ነው እዚህ የደረስነው፣ጉዳዩ ከአዴንም አልፎ የህዝብ አጀንዳ ነው፣ ስም ማጥፋት ነው የያዙት በተለይየሸንጎው ሊቀመንበር ስም ማጥፋት ነው የያዘው ጉዳዩም አይመለከተውም ፣ መግለጫም ማውጣት ያለበት ስለራሱ ጉዳይና ይወክለኛል ስለሚለው ህዝብ ነው፣ በአስተሳሰብ፣ በስልትና በአላማ በከፍተኛ ደረጃ እንለያያለን፡፡” ነው ያሉት፡፡

የሰላም ውይይቱን በተመለከተ ከአገው ሸንጎ ሊቀመንበር ጋር እንደተነጋገሩና በሰቆጣው ውይይት ላይ እንዲገኙ ተስማምተን ነበር የሚሉት አቶ ኪሮስ ሆኖም ሊቀመንበሩ በስም ማጥፋት ላይ ተሰማርተዋል፣ በማህበራዊ ሚዲያም የማይሆን መልዕክት እየፃፉ ነው ሲሉም ከስሰዋል፡፡

የአገው ብሄራዊ ንቅናቄ ጋዜጣዊ መግለጫ
የሰላም ውይይቱን በተመለከተ ከአገው ሸንጎ ሊቀመንበር ጋር እንደተነጋገሩና በሰቆጣው ውይይት ላይ እንዲገኙ ተስማምተን ነበር የሚሉት አቶ ኪሮስ ሆኖም ሊቀመንበሩ በስም ማጥፋት ላይ ተሰማርተዋል፣ በማህበራዊ ሚዲያም የማይሆን መልዕክት እየፃፉ ነው ሲሉም ከስሰዋል፡፡ምስል Seyoum Getu/DW

“ምንም ቢሆን የአገው ህዝብን ጉዳይ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ያለ አካላ ነው ብለን ጠርተን አነጋገርን፣ በጣም ደስ ብሎት፣ በሰቆጣው ስነስርዓት ላይ እንዲገኝ ተጋብዞ እሽ ካለ በኋላ በቅፅበት ተቀይሮ በፌስ ቡክ የተለያዩ ጉዳዮችን እየፃፈ ነው፣ ጉዳዩ አይመለከተውም ነገሩንም በሚገባ አያውቅምወንጀልም ነው እንደዚህ አይፃፍም፡፡”

የአገው ብሔራዊ ሸንጎ ሊቀመንበር አቶ አላምረው ይርዳው በሰቆጣው ውይይት የተጋበዝሁት እንደግለሰብ እንጂ በይፋ ለፓርቲው ጥሪ አልተደረገለትም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡የ7 ቤት አገው የፈረሰኞች ማህበር በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ተጠየቀ  

የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ከ2013 ዓ ም ጀምሮ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አበርገሌና ፃግብጂ ወረዳዎች በትጥቅ ትግል ከመንግስት ጋር ሲዋጋ የነበረ ድርጅት ነው፡፡ የአገው ብሔራዊ ሸንጎ ደግሞ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና የተሰጠው የፖለቲካ ድርጅት ነው፡፡

የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄና የአማራ ክልል መንግስት ያደረጉትን የሰላም ስምምነት በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች የጋራ ምክር ቤት በአወንታዊ እንደተቀበለው ሰሞኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ታምራት ዲንሳ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር