1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአድዋ ድል በዓል አከባበር ዉዝግብና የህዝብ አስተያየት

ዓርብ፣ የካቲት 22 2016

ከኢትዮጵያውያን አልፎ የጥቁር ህዝብ ድል ተደርጎ የሚነሳው የአድዋ ድል በዓል በአንድነት እና በህብረት እንዲከበር አስተያየት ሰጪዎች ጠየቁ፡፡ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ እየጎላ የመጣው ውዝግብ መወገድ አለበት

https://p.dw.com/p/4d5P8
ከቅርብ ጊዜ ወዲሕ በአድዋ ድል መታሰቢያ በዓላት ላይ የሚነሳዉ ዉዝግብ አሳሳቢ እየሆነ ነዉ።
የአድዋ ድል መታሰቢያ አርማምስል Seyoum Getu/DW

የአድዋ ድል በዓል አከባበር ዉዝግብና የህዝብ አስተያየት

ከኢትዮጵያውያን አልፎ የጥቁር ህዝብ ድል ተደርጎ የሚነሳው የአድዋ ድል በዓልበአንድነት እና በህብረት እንዲከበር አስተያየት ሰጪዎች ጠየቁ፡፡ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች  እንዳሉት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ እየጎላ የመጣው ውዝግብ መወገድ አለበት።128ኛው የአድዋ ድል በዓል፣ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ አከባቢዎች ነገ ይከበራል።አምና 127ኛው የድል በዓልሲታሰብ በተለይም ፒያሳ በሚገኘው የሚኒሊክ አደባባይ አከባቢ በተፈጠረው  ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በርካቶች በአስለቃሽ ጭስ መበተናቸው አይዘነጋም፡፡

ስዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ