1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ኅብረት ዩክሬንና ሞልዶቫ ለአባልነት ድርድር እንዲጀምሩ ፈቀደ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 29 2016

ህብረቱ ቱርክን ጨምሮ ለሌሎች 5 አገሮች ጥያቄ ለዓመታት ምላሽ ሳይሰጥ የዩክሬንና ሞልዶቫ ጥያቄ በፍጥነት መፍቀዱ አነጋጋሪ ሁኗል። ሁለቱ ሀገራት ለእባልነት መስፈርቶችን በበቂ ሁኒታ ከማሟልታቸው ይልቅ ዩኪሬን ከሩሲያ ጋር በምታካሂደው ጦርነት ሰበብና የፖለቲካ ውሳኔም የታክለበት ሳይሆን እንዳልቀረ ታዛቢዎች ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/4Ycgn
ዑርዙላ ፎን ደርላይን የአውሮጳ ኅብረት ኮሚሽነር
ዑርዙላ ፎን ደርላይን የአውሮጳ ኅብረት ኮሚሽነር ምስል John Thys/AFP

ህብረቱ ቱርክን ጨምሮ ለሌሎች 5 አገሮች ጥያቄ ለዓመታት ምላሽ ሳይሰጥ የዩክሬንና ሞልዶቫን ጥያቄ በፍጥነት መፍቀዱ አነጋግሯል።

የአውሮጳ ኅብረት ኮሚሺን፤ ዩክሬንና ሞልዶቫ የኅብረቱ ሙሉ አባል ለመሆን የሚያስችላቸውን ድርድር እንዲጀምሩ ፈቀደ። ሁለቱ የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ግዝት አካል የነበሩ አገሮች፤ የአውሮጳ ኅብረት አባል ለመሆን በይፋ ጥያቄ ያቀረቡት ከአንድ አመት በፊት የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት እንደተጀመረ ነበር። ህብረቱም በፍጥነት ማመልከቻቸውን ተቀብሎ፤ በእጩ  አባልነት ይዟቸው ከቆየ ብኋላ፤ ትናንት የመግቢያ ድርድር እንዲጀምሩ ኮሚሽኑ ድጋፉን የሰጠ መሆኑ የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ኡርዙላ ፎንደርለየን አስታውቀዋል .

የአውሮጳው ኅብረት በአዲስ ኣባላት መስፋፋት“ ዛሬ ዩክሬንና  ሞልዶቫ የህብረቱ አባል ለመሆን የሚያስችላቸውን ድርድር እንዲጀምሩ በይፋ ድጋፍ የተስጠበት  ታሪካዊ ቀን ነው በማለትም ውሳኔውን ይፋ አድርገዋል።   በተጨማሪም  ቦዝኒያ ሄርዞጎቪና  ማሟላት የሚገባትን መስፈርቶች ካሟላች  እንደዚሁ የመግቢያ  ድርድሩን እንድትጀምር እንደተወሰናና  ጆርጂያም በእጩ አባልነት እንድትያዝ ሀሳብ የቀረበ መሆኑን ወይዘሮ ፎንዴርልየን አክለው ገልጸዋል።የአውሮጳ ህብረት አባል ለመሆን በርካታ የመግቢያ መስፈርቶችን ማሟላት ግዴታ ሲሆን፤ እጩ አባል አገራቱ የሚጠበቅባቸውን የህግና  የፖሊስ ማሻሻያዎችን  በሚፈለገው ልክ መፈጸማቸውን በተራዘመ ድርድርና ውይይት ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል።

ህብረቱ እ እ እበ2013 ም ክሮሺያን በአባልነት ከተቀበለ ወዲህ ቱርክን ጨምሮ የሌሎች አምስት አገሮችን ጥያቄ ለአመታት ምላሽ ሳይሰጥ ፤ የዩክሬንና ሞልዶቫ ጥያቄ በፍጥነት እዚህ ደረጃ መድረሱ አነጋጋሪ ሁኗል።
ውሳኔው ግን  እ እ እ ከ1999 አም ጀምሮ እጩ አባል በሆነችው ቱርክና ሌሎችም እገሮች ቅሬታ  እንደሚፈጥር የሚገመት፤ ሲሆን ሁሉም ሀያ ሰባቱ አባል አገሮችም የኮሚሽኑን የተፋጠነ እርምጃ በፍጥነትና  በደስታ በሙሉ ድምጽ መቀበላቸውም አጠራጣሪ ነው።ምስል Ukraine Presidency/Ukrainian Pre/Planet Pix/ZUMA Press Wire/picture alliance

የመግቢያ ድርድሩን ለመጀመርም እንዲሟሉ የሚፈለጉ አሰራሮችና የማሻሻያ ፕሮግርሞች ያሉ መሆኑን ያወሱት ወይዘሮ ፍቮንዴርለየን፤ ዩኪረን በጦርነት ውስጥም ሆና አሳክታቸዋለች ያሉዋቸውን ፕሮግራሞች ጠቅሰዋል፤ “ በህገመንግስት ማሻሻያ ፕሮግርሞች፣ በዳኖችች አመራርጥ፤ የጸረ ሙስና ህግ በማውጣት፤ የህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን በመቆጣጠርና  አዲስ የሜዲያ ህግ በማውጣት ትልቅ ለውጥ ታይቷል በማለት በሌሎች በቀሩ ጥቂት ፕሮግራሞችም በቅርቡ ለውጥ እንደሚደረግ ያላቸውን እምነት ገልጸው፤ በነዚህ ምክኒያቶች ኮሚሽኑ ለዩክሬን የመግቢያ ንግግሩ በር እንዲከፈት የጠየቀ መሆኑን አስታውቀዋል፡፤ ሞልዶቫም  እንደ ዩኪሬን ሁሉ በችግር ውስጥ ሁና በርክታ የማሽሻሻያ እርምጃዎችን የወሰደች በመሆኑ ለሷም ተመሳሳይ ዕድል የተሰጠ መሆኑን ወይዘሮ ቮንዴርሌየን ገልጸዋል።የቱርክ ትብብር እና የአውሮጳ ኅብረት ጥያቄ

ውሳኔው በተለይ በጦርነት ውስጥ ላለቸውና ጦርነቱ በመራዘሙ ምክኒያት የሚደረግላት ድጋፍ እንዳይቀንስ ስጋት ለገባት ዩኪሬን ትልቅ የሞራል ስንቅ ሆኖ ተወስዷል፡፤ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በማህበራዊ ገጻቸው ውስኔውን ታሪክዊ በማለት አገራቸው የህብረቱ አካል መሆን የሚገባት መሆኑንና በጦርነት ውስጥም ሆና የሚያስፈልጉትን ለወጦች እያደረገች መሆኑን ጠቅሰው ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ ህብረቱ እ እ እበ2013 ም ክሮሺያን በአባልነት ከተቀበለ ወዲህ ቱርክን ጨምሮ የሌሎች አምስት አገሮችን ጥያቄ ለአመታት ምላሽ ሳይሰጥ ፤ የዩክሬንና ሞልዶቫ ጥያቄ በፍጥነት እዚህ ደረጃ መድረሱ አነጋጋሪ ሁኗል። የዩክሬንም ሆነች ሞልዶቫ በዚህ ፍጥነት ለእባልነት መቃረባቸው መስፈርቶችን በበቂ ሁኒታ ከማሟልታቸው ይልቅ በተለይ ዩኪሬን ከሩሲያ ጋር በባችበት ጦርነት  ምክኒያት ሊሆን እንደሚችልና የፖለቲካ ውሳኔ የታክለበት ሳይሆን እንዳልቀረ ታዛቢዎች ይናገራሉ።የአውሮጳ ኅብረት የመስፋፋት እቅድና አንድምታው 

ህብረቱም በፍጥነት ማመልከቻቸውን ተቀብሎ፤ በእጩ  አባልነት ይዟቸው ከቆየ ብኋላ፤ ትናንት የመግቢያ ድርድር እንዲጀምሩ ኮሚሽኑ ድጋፉን የሰጠ መሆኑ የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ኡርዙላ ፎንደርለየን አስታውቀዋል .
ሁለቱ የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ግዝት አካል የነበሩ አገሮች፤ የአውሮጳ ኅብረት አባል ለመሆን በይፋ ጥያቄ ያቀረቡት ከአንድ አመት በፊት የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት እንደተጀመረ ነበር። ምስል Eric Vidal/EU

 የፍራንስ  24 ቴለቪሽን ጋዜጠኛና  ያውሮፓ ጉዳይ አዘጋጅ አርመን ጂዮርጂያ እንደሚለው፤ ምንም እንኳ መስፈርቱ ለሁሉም እጩ አገሮች አንድ አይነትና እኩል ቢሆንም፤ የሁለቱ አገሮች ሁኔታ ግን የተለየ ነው፤ “ ዩክሬንና ሞልዶቫን በሚመለክት  የፖለቲካ ውሳኔ የለበትም ማለት አይቻልም።  ኮሚሽኑም ሆነ ህብረቱ ለእነዚህ ሁለት አገሮች ላለፈው አንድ አመት ተኩል ድጋፋቸውን ሲሰጡ ነው የከረሙት በማለት በደህንነት  ምክኒያት ሁለቱ አገሮች በታቻለ ፍጥነት የህብረቱ አባሎች እንዲሆኑ ይፈለግ ነበር ብለዋል።

ውሳኔው ግን  እ እ እ ከ1999 አም ጀምሮ እጩ አባል በሆነችው ቱርክና ሌሎችም እገሮች ቅሬታ  እንደሚፈጥር የሚገመት፤ ሲሆን ሁሉም ሀያ ሰባቱ አባል አገሮችም የኮሚሽኑን የተፋጠነ እርምጃ በፍጥነትና  በደስታ በሙሉ ድምጽ መቀበላቸውም አጠራጣሪ ነው። ያም ሆኖ የህብረቱ መሪዎች በታህሳሱ ስብሰባቸው የኮሚሽኑን ውሳኔ ተቀብለው ሁለቱ አገሮች የመግቢያ ድርድሩን እንዲጀምሩ የቀረበውን ጥያቄ ቢይጸድቁም፤ የአባልነት መስፈርትን አሟልቶ ለመገኘት ለበርክታ ወራት መገምገምና በተራዘሙ ድርድሮች ማለፍ አስፈላጊ በመሆኑ ዩክሬንና ሞልዶቫ የህብረቱ ሙሉ አባል ለመሆን   አሁንም አመታትን ሊጠብቁ ይችላሉ ነው የሚባለው።

ገበያው ንጉሤ

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ