1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ኅብረት ውሳኔዎች በዓለም አቀፍ የፀጥታ ጉዳዮች

ማክሰኞ፣ ሰኔ 18 2016

የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት ሉክዘምበርግ ውስጥ ባካሄዱት ስብሰባቸው እንደተለመደው ለዩክሬን እና ለጋዛ ቅድሚያ ሰጥተው በመወያየት ውሳኔዎችን አሳልፈዋል ።

https://p.dw.com/p/4hUUW
Rat der Aussenbeziehungen in Luxemburg
ምስል Thomas Koehler/AA/picture alliance

ለዩክሬን የሚሰጠው ርዳታ ተጠናክሮ የሚቀጥል ስለመሆኑ

የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት ሉክዘምበርግ ውስጥ ባካሄዱት ስብሰባቸው እንደተለመደው ለዩክሬን እና ለጋዛ ቅድሚያ ሰጥተው በመወያየት ውሳኔዎችን አሳልፈዋል ። ከጆሪጂያና የምራብ ባልካን አገሮች ጋር ስላለውና ስለሚኖረው ግንኙነት በተመለከተም ተወያይተዋል ። ስለ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ  ቀውስና የሱዳን ጉዳይ ላይም ተነጋግረው ውሳኔዎችን አሳልፈዋል። 

የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሰኔ 2016 (2024) ስብሰባና አጀንዳዎች የሀያ ሰባቱ ያውሮጳ ኅብረት አገሮች  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት በሉክዘምበርግ ባካሄዱት የሰኔ ወር ስብሰባቸው እንደተለመደው ዩኪረንና ጋዛን ቅድሚያ ሰተው በመወያየት ውሳኔዎችን አሳልፈዋል። ሚኒስትሮቹ ከሁለቱ የዚህ ዘመን የህብረቱ ቋሚ አጀንዳዎች በተጨማሪ ካውሮፓ ከጆሪጂያና የምራብ ባልካን አገሮች ጋር ስላለውና ስለሚኖረው ግንኑነት፤ ካፍርካ በታላቁ የህይቅ አካባቢ በተለይም በዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ  ባለው ቀውስና ሱዳን ላይም ተወይይተው ውስኔዎችን አሳልፈዋል።

ለዩክሬን የሚሰጠው ርዳታ ተጠናክሮ የሚቀጥል ስለመሆኑ

በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ላይ ሚኒስትሮቹ ባካሄዱት ውይይት፤  በመሬት ላይ ያለውን ወታደራዊ ሁኔታና ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እየፈጸሙት ነው የተባለውን መጠነ ሰፊ ጥቃት እንደተረዱና ወታደራዊ ርዳታውን አጠናክረው ለመቀጠልም የተስማሙ መሆኑን ሚስተር ቦርየል የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊና የስብሰባው መሪ አስታውቀዋል። ለዩክሬን እየተሰጠ ያለውን ወታደራዊ ደጋፍ  እንደገና አጢነናል። ዛሬ በዩክሪን በተጨባጭ የሚያስፈልገው ተጨማሪ ወታደራዊ ዕርድታ ነው፤ ተጨማሪ  ያየር መቃወሚያዎችን፤ ተተኳሾችን ማቅረብና የራሷን  እንዱስትሪ አቅምም መገንባት ነው”  በማለት አባል መንግስታቱ፤ ህብረቱ ባጠቃላይ  ለዚህ ቁርጠኖች መሆናቸውን ገልጸዋል፤ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩኪሬን የሚፈጽሙትን ጥቃት አጠናክረው ሲቀጥሉ፤ የህብረቱ እርዳታ ሊነጥፍ ወይም ሊቀንስ ይችላል ብለው አስበው ከሆነ የተሳሳቱ መሆኑን በመግለጽ ጭምር።

በሩሲያ ላይ የተወሰዱ ተጨማሪ የማዕቀብ ርምጃዎች

 በቁልፍ የሩሲያ የኢኮኖሚ አውታሮች በተለይም በኢኔርጂ ዘርፉ ያተኮሩ ተጨማሪ የማቀብ እርምጅዎች የተላለፉና፤ በህብረቱ ባንኮች እንዳይንቀስቀስ ከታገደው የሩሲያ ሀብት የሚገኘው ትርፍም ለዩኪሬን እንዲሰጥ የተወሰነው ውሳኔ ተግብራዊ ሊሆን የሚችልበት የህግ አግባብና አሰራር እንደተዘርጋም አስገንዝበዋል።

ለዩክሬን የሚሰጠው ርዳታ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ ተነግሯል
ለዩክሬን የሚሰጠው ርዳታ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ ተነግሯልምስል Annegret Hilse/REUTERS

የጋዛ ሰብአዊ ቀውስ ቀጣይነትና የመዛመት ዕድሉ 

በመካከለኛው ምስራቅ ላይ በተክሄደው ውይይት፤ ሚኒስትሮቹ በአክባቢው በአጠቃላይ፤ በተለይ ደግሞ በጋዛ ስላለው ሰባዊ እልቂትና ውድመት የተወያዩና ችግሩን የተገንዘቡ መሆኑ ተገለጸ ቢሆንም፤  ከችግሩ ስፋትና ካለው ሰባዊ ቀውስ አንጻር የተመጣጠነ እርምጃ የወሰዱ ወይም ለመውሰድ ሚኒስትሮቹ የተስማሙ ስለመሆኑ በይፋ አልተገለጸም። ይልቁንም ሚስተር ቦርየል  ክስብሰባው በኋላ በሰጡት መግልጫ፤ " ከሶስት ሳምንት በፊት ከአሜርካ የቀረበውና የአውሮፓ ህብረትን ድጋፍ ያገኘው የሰላም ሀሳብ ከሁለቱም ወገኖች አዎንታዊ ምላሽ እላገኘም” በማለት በዚህም ምክኒያት የጋዛ ህዝብ ስቃይ እንዳይቀጥልና የታጋቾችም የነጻነት ግዜ እሩቅ እንዳይሆን የሚይሰጋ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪም ባሁኑ ወቅት ግጭቱ  ወደሌሎች  አክብቢዎች እንዳይዛመት የሚያሰጋ መሆኑን በመገንዘብ ሚኒስትሮቹ ለእርዳታ መግብት፣ ለታገቱ መለቀቀቅና ለዘላቂ ስላም፤ የተኩስ ማቆም ስምምነት ወስኝ በመሆኑ ህብረቱ በዚህ በኩል ጥረቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል የተስማሙ መሆኑን ሚስተር ቦርየል አክለው ገልጸዋል። 

የሚንስትሮቹ ስብሰባ በዚህ ወቅት ከዩክሬንና መካከለኛው ምስራቅ ውጭ፤ በአፍሪካ የታላቁ ሀይቅ አክባቢ፤ በተለይም በዲሞርክሲይዊ ሪፑብሊክ ኮንጎ ስላለው ግጭትና ሰባዊ ቀውስ ተወያይተዋል። የችግሩን አሳስቢነት በመረዳትም  ሁኒታውን በቅርብ ለመክታተልና የሚቻለውን  ለማድረግ የአካባቢው የህብረቱ ልዩ መልክተኛ እንዲመደብ ከስምምነት እንደተደርሰና መልክተኛውም በቅርቡ ወደ አካባቢው የሚላክ ስለመሆኑም ተገልጿል።

በሱዳን ጀነራሎች ላይ የተላለፈው ማዕቀብ

በጉባኤው ስለ ሱዳን ጉዳይም ተነስቶ ውይይት ተደርጓል
በጉባኤው ስለ ሱዳን ጉዳይም ተነስቶ ውይይት ተደርጓልምስል AFP

በዚህ ስብሰባ ብዙም ትኩረት ሳይስጠው ስለቆየው የሱዳን የርስ በርስ ጦርነትና ቀውስ ውይይት ተደርጎ የሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችን ጨምሮ ተጨማሪ ስድስት ግለሰቦች የማዕቀብ ውሳኔ የተላለፈባቸው መሆኑ ታውቋል። በምዕራብ ዳርፉር የጄነራ\ል ዳጋሎ የፈጥኖ ደራሽ ጦር አዛዥ አብዱልራህማን ጁማ ባራካአላህ፤  በዳርፉር በተፈጸመውና እየተፈጸመ ባላው ግድያና የሰባዊ መብት ጥሰት፤ በጄኔራል አልቡርሀን በሚመራው የሱዳን ጦር በኩል  ያየር ሀይሉ ዋና አዛዥ ኤልጣሂር ሞሃመድ ኤል አዋድ  በጅምላ እየተፈጸመ ባለ ያየር ድብደባ፤ የማዕቀብ ውሳኔ ከተላለፈባቸው በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው። ማዕቀቡ፤ ንብረት እንዳይንቀሳቀስ ማገድንና የጉዞ ክልከላን የሚያጠቃልል ነው ተብሏል ።

ገበይው ንጉሤ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ