1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ምርጫዎች ውጤት አንደምታ በአውሮጳና አፍሪቃ ግንኙነት

ሐሙስ፣ ሰኔ 27 2016

በአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ የተገኘው ያክራሪና ብሂረተኖች ድል፤ ያባል ገሮችን ፖለቲክንም ማናወጥ ይዟል። በቤልጅየም መንግስት አፈርሷል፤ በፈረንሳይ አስቸኳይ ምርጫ እንዲደረግ አስገድዷል።

https://p.dw.com/p/4hsI3
Europawahl Berlin Afd Wahlparty
ምስል FILIP SINGER/EPA

የአውሮጳ ምርጫዎች ውጤት አንደምታ በአውሮጳና አፍሪቃ ግንኙነት

ባለፈው የሰኔ ወር መጀመሪያ ሳምንት በ27ቱም የአውሮፓ ህብረት አገሮች የተካሂደው የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫና ውጤቱ  አውሮፓን እያናወጠው ነው። የአውሮጳ ኅብረትን አካሄድ የሚቃወሙ ፀረ የአውሮፓ ኅብረት ኃይሎች፣ ስደተኞችንና ከአውሮፓ ውጭ ዝርያ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የማህበራዊ ችግሮች ምንጭ አድርገው የሚቆጥሩ አክራሪ ቡድኖች፤ ያየር ለውጥ የደቀነውን ስጋት አቅለው የሚያዩ ሀይሎች፤ ባውሮፓ እንደ ዘንድሮ ተሳክቶላቸው አያውቅም፤ በሁሉም አባል አገሮች ከፍተኛ ድምጽ አግንተው  በአውሮፕ ፓርላማ ትልቅ ቡድን ለመሆን በቅተዋል።  በአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ የተገኘው  ያክራሪና ብሂረተኖች ድል፤ ያባል ገሮችን ፖለቲክንም ማናወጥ ይዟል።የአውሮጳ ኅብረት ምክር ቤት ምርጫ ውጤትና አንድምታው

በቤልጅየም መንግስት አፈርሷል፤ በፈረንሳይ  አስቸኳይ ምርጫ እንዲደረግ አስገድዷል። ባለፈው ሳምንት በተካሂደው የመጀመሪያው ዙር ምርጫ አሁንም የወይዘሮ ሌፔን በእንግልዚኝ ምሃጻሩ ( RN ) አክራሪ ብሄረተኛ  ፓርቲ ትልቁ ፓርቲ ሆኖ የወጣ ሲሆን፤ በሚቀጥለው  ዕሁድ በሚደረገው ሁለተኛው ዙር ምርጫም ይኸው ፓርቲ ትልቁ ፓርቲ ሆኖ መውጣቱ እንደማይቀር ነው የሚገመተው። ባጠቃላይም ያውሮፕ ፓርላማ ምርጫ ውጤትም ሆነ በብዙዎቹ አባል አገሮች  ያሉት አክራሪና ብሄረተኛ ፓርቲዎች እየጎልበቱና  እያሸንፉ መምጣታቸው፤ ያውሮፓን ፖለቲካ  ወደቀኝ እንዲያዘነብል አድርጎታል እየተባለ ነው። ይህ ማለት   ያውሮፓ ፓርላማ በሚያራምዳቸው የህብረቱን አንድነት ማጎልበቻና ማጠናከሪያ ፕሮግራሞች፣ በአየር ንብረት ለውጥ አጀንዳ ፣ በስደተኖችና የውጭ ግንኑነቶች ፖሊስዎች ላይ ለውጥ ሊኖር ይችላል ማለት ነው እንደ ብዙ ባለሙያዎች አሰተያየት ።

በፈረንሳዩ የፓርላማ ምርጫ ያሸነፈው ቀኝ ጽንፈኛ ፓርቲ መሪ ማሪ ለፔን
በፈረንሳዩ የፓርላማ ምርጫ ያሸነፈው ቀኝ ጽንፈኛ ፓርቲ መሪ ማሪ ለፔንምስል Yves Herman/REUTERS

የአውሮፓ ህብረት በድህረ-ምርጫ

የቀኝ ጽንፈኞች በፈረንሳይ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ማሸነፍ አንድምታ
ዲደብሌው ያውሮፓ የልማት ፖሊሲ ማዕከል በእንግሊዝኛ  ምህጻሩ (ecdpm) የተሰኘውን፤ በተለይ ባውሮፓና አፍርካ ግንኙነቶች ላይ የሚሰራ መንግስታዊ ያልሆነ  ድርጅት ተባባሪ ዳይሬክተር የሆኑትን ዶክተር ሳን ቢላልን፤ የአውሮፓ ምርጫዎች ውጤት በህብረቱና  አፍሪካ ግንኑነትና ትብብር ላይ ሊያሳድረው ስለሚችለው ተጽኖ አነጋግሯቸዋል።  ዶክተር ቢላል፤ ምርጫው  አዳዲስ የሀይል አሰላለፎችን ሊፈጥርና ያጀንዳ ቅደም ተከትሎችንም ሊያስቀይር እንደሚችል በመጥቀስ፤  በመጭዎቹ አመታት ህብረቱ ውዴት ሊይዘነብል እንደሚችል  ገልጸዋል። “ በትክክክል ወደቀኝ የሚያደላ ነው የሚሆነው። የያገሮቻቸውን ሉላዊነት የሚያስቀድሙ ፖለቲከኖች አጀንዳዎቻቸውን ቅድሚያ የሚያሲዙበት ነው የሚሆነው” በማለት የህብረቱን ድህረ ምርጫ አቅጫ ጠቁመዋል። ዶክተር ቢላል አክለውም በአለም ካለው ለውጥና ምርጫውም ካስተላለፈው መልክት አንጻር በድህረ ምርጫ፤ “ ለራሱ ትኩረት የሚሰጥ አውሮፓን፣ በራሱ የእንዱስትሪ መስፋፋት ላይ ትኩረት የሚያደርግ አውሮፓን፤ ለስራ ፈጠራ ትኩረት የሚሰጥንና ደንበሮቹን የሚያጠብቅ አውሮፓን ልናይ እንደንችላለን ብለዋል።

የአውሮጳ ፓርላማ ምርጫ
የአውሮጳ ፓርላማ ምርጫ ምስል Andreea Alexandru/AP Photo/picture alliance

የበጀት ቅናሽ ሊያስከትል ስለመቻሉና የስደተኞች ጉዳይ

 

ሚስተር ቢላል ይህ ምርጫ በህብረቱ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተግዳሮቶችች ሲገልጹም፤ “ የአውሮፓ ህብረት በጀት፤ ለልማት እርዳታ የሚስጠው በጀት ጭምር አሁን ካለው ሊቀንስ ይችላልም” ብለዋል ። ስደተኖችን በሚመለከትም እርዳታ ልንሰጥ የምንችለው ተመላሽ ስደተኖችን ስትቀበሉ ነው የሚሉ ቅድመ ሁኔትዎችን ህብረቱ ሊያስቀምጥ እንደሚችል የገለጹት ዶክተር ቢላል፤ ያም ሆኖ ግን  ለስደት በሚያስገድዱ ሁኔታዎችና ችግሮች ላይ ላይ ካልተሰራ በስተቀር   ምንም ያህል ቅድመ ሁኔታ ይቀመጥ ወይም አጥር  ይገንባ  ስደተኖችነ ማስቆም ኧንደማይቻል  አጽናኦት ሰተው ተናግረዋል  የአውሮጳ ምክር ቤት የምርጫ ውጤት እየፈጠረ ያለው ቀውስ

የፈረንሳይ ምርጫ ውጤት ቢሆኖች

በመጨረሻም ዶክተር ቢላልን  በሚቀጥለው ሳምንት በፈረንሳይ በሚደረገው ምርጫ የወይዘሮ ሌፔን ፓርቲ  አሸንፎ ቢወጣ ሊሆን የሚችለውን አስመልክቶ ግምታቸውን ተጠይቀው ሲመልሱ “ ሁለት ቢሆኖችን ማስቀመጥ ይቻላል፤  አንደኛው የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስተር ሜሌኖ መንግስት  አይነት ነው፡፤ እሳቸው ወደ ስልጣን የመጡት በብሄረተኛ አጀንዳ ቢሆንም፤ ስልጣን ክያዙ በሁላ ግን ተግባራዊ ሊሆኑ በሚችሉ አጀንዳዎች ላይ በማተኮር ወደ መሀል ሲቀርቡ ነው የተስተዋሉት።ይህም ማለት አክራሪ ፓርቲዎች ስልጣን ከያዙ በኋላ ወደ መሀል የመምጣት ዕድል እንዳላቸው የሚያመላክት ነው። ሆኖም ግን በፈረንሳይ የተለየ ሊሆንም ይችላል በማለት ህዝቡን አሳምነው ከመጡና ካሸነፉ በኋላ  የተመረጡበትን አጀንዳ ሊያስቀጥሉና ለውሮፓ ህብረት የሚሰጡትን ገንዘብ ሊቀንሱ፤ በስደተኖች ላይ ጥብቅ ህግ ሊያወጡና የፈረንሳዮች ዋና መለያ የሆኑት የየነጻነት፣ ወንድማማችነትና ዕኩልነት መፈክሮችም አነስተኝ ግምት ሊሰጣቸው  ይችላል ብለዋል  
ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሰ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር