1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአከራይ ተከራይ ሕግ፡ የህዝብ አስተያየት

ረቡዕ፣ መጋቢት 25 2016

«የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ» የተሰኘው ሕግ ግልጽነት፣ ተጠያቂነት፣ ወጥነት እና ተገማችነት ያለው፣ የአከራይ እና ተከራይን መብት ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ለማስተዳደርና ዘርፉን በሕግ ለመምራት ታስቦ መዘጋጀቱም ተነግሯል።

https://p.dw.com/p/4eOll
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አዲስ ሥለወጣዉ የመኖሪያ ቤት ሕግ ያላቸዉ አስተያየት የሚቃረን ነዉ።
የአዲስ ከተማ በከፊል።የኢትዮጵያ መንግስት ያወጣዉ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ሕግ ለአከራይና ተከራይ ሚዛናዊ ነዉ ተብሏልምስል Solomon Muchie/DW

የአከራይ ተከራይ ሕግ፡ የህዝብ አስተያየት

የኢትዮጵያ  የአከራይ ተከራይ ህግ ከትናንት ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውል ተደርጎ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል፡፡«የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርእና አስተዳደር አዋጅ» የተሰኘው ሕግ ግልጽነት፣ ተጠያቂነት፣ ወጥነት እና ተገማችነት ያለው፣  የአከራይ እና ተከራይን መብት ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ለማስተዳደርና ዘርፉን በሕግ ለመምራት ታስቦ መዘጋጀቱም ተነግሯል።ይህ አዋጅ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማበመኖሪያ ቤት እጦትለተቸገሩ እና በየጊዜው አከራዮች የዋጋ ጭማሪ  ለሚያደርጉባቸዉ ተከራዮች ጠቃሚ የሚሉ ያሉ እንዳሉ ሁሉ፤ ችግሩ በዚህ ብቻ አይፈታም ያሉም በርካቶች ናቸው፡፡አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬለ የሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ሥለ ህጉ የተለያየ ሐሳብ አንፀባርቀዋል።

ስዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ