1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአቶ ልደቱ የዋስትና መብት አከራከረ

ማክሰኞ፣ መስከረም 19 2013

ማክሰኞ፦ መስከረም 19 ቀን፣ 2013 ዓ.ም ያስቻለው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአቶ ልደቱ አያሌው የዋስትና እግድ ውሳኔ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል። አቃቤ ሕግ እና የአቶ ልደቱ  ጠበቃ የዋስትና መብት ይከበር አይከበር በሚል ዛሬ ተከራክረዋል።

https://p.dw.com/p/3jAr1
Äthiopien Pressekonferenz EDP in Addis Abeba
ምስል DW/G. Tedla

ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተይዟል

ማክሰኞ፦ መስከረም 19 ቀን፣ 2013 ዓ.ም ያስቻለው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአቶ ልደቱ አያሌው የዋስትና እግድ ውሳኔ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል። አቃቤ ሕግ እና የአቶ ልደቱ  ጠበቃ የዋስትና መብት ይከበር አይከበር በሚል ዛሬ ተከራክረዋል። የዛሬ የችሎት ቀጠሮ የተያዘው የምሥራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለአቶ ልደቱ የመቶ ሺህ ብር ዋስትና ፈቅዶ የነበረ ቢኾንም ዋስትናው እንዲታገድ በአቃቤ ሕግ በመጠየቊ እንደነበር ተገልጧል።  በችሎቱ  ታድመው የነበሩትን የኢዴፓ ሊቀመንበር አቶ አዳነ ታደሰን በስልክ ያነጋገረው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ቀጣዩን አጠናቅሯል።  

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶትስ ስለሺ
ኂሩት መለሰ