የአርቲስቱ ሀውልት ዛሬ ተመረቀ
እሑድ፣ ጥቅምት 15 2013ማስታወቂያ
በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ቀደም ሲል በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ስም ከተሰየመው ካምፓስ ፊትለፊት የተገነባው የአርቲስቱ ሀውልት ዛሬ ተመረቀ። በሃውልቱ የምርቃት ስነ ስርአት ላይ የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ጓደኞችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል። የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ታደሰ ቀነአ በሃውልቱ ምርቃት ላይ እንዳሉት አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ለማስታወስ የተገነባዉ ሃዉልቱ "አርቲስቱ ለህዝብ ነጻነት ያደረገውን ተጋድሎ የሚያስታዉስ ነው" ብለዋል፡፡ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር መንግስቱ ቱሉ ለዶይቼ ቨለ እንደተናገሩት ሃዉልቱ የአርቲስቱን የሕይወት ዘመን ታሪክ እና አስተዋፅኦን ታሳቢ አድርጎ የተገነባ ነው ብለዋል:: የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ አፅም ባረፈበት በአምቦ እየሱስ ቤተክርስቲያን የተገነባዉ የመታሰቢያ ሃዉልት ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል.
ታምራት ዲንሳ