1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

የአሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤት ስለ ትግራይ ግጭት 

ረቡዕ፣ ሰኔ 23 2013

ለትግራይ ክልል ቀውስ ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኘት ሁሉም ኃይሎች ለተኩስ አቁም ስምምነት መገዛት እንደሚጠበቅባቸው በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳዮች ተጠባባቂ ረዳት ሚኒስትር አሳሰቡ።

https://p.dw.com/p/3vpAY
Washington Kapitol am Abend
ምስል J. Scott Applewhite/AP/picture alliance

የአፍሪቃ ጉዳዮች ተጠባባቂ ረዳት ሚኒስትር

ለትግራይ ክልል ቀውስ ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኘት ሁሉም ኃይሎች ለተኩስ አቁም ስምምነት መገዛት እንደሚጠበቅባቸው በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳዮች ተጠባባቂ ረዳት ሚኒስትር አሳሰቡ። የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት አስመልክቶ ትናንት ምስክርነት ባዳመጠበት ወቅት ተጠባባቂ ረዳት ሚኒስትሩ እንዳሉት፦ የኢትዮጵያ መንግስት በተናጠል የወሰደው የተኩስ አቁም ርምጃ አበረታች ሲሆን ሌሎቹም ኃይሎች ለስምምነት መገዛት ይጠበቅባቸዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የየልማት ድርጅት ረዳት አስተባባሪ ሣራ ቻርልስ በበኩላቸው በትግራይ ከሰብዓዊ ርዳታ ተደራሽ ያልሆኑ የሆኑ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ለመድረስ ይቻል ዘንድ የአቅርቦት መስመሮች እንዲከፈቱ ጥሪ አቅርበዋል። 

ታሪኩ ኃይሉ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሀመድ