1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የንግድ ባንክ ገንዘብና ተማሪዎች

ረቡዕ፣ መጋቢት 11 2016

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፈዉ አርብ የኮምፒዊተር ሥርዓት ችግር አጋጥሞት የገንዘብ ወጪና የዝዉዉር ሥርዓቱ ተናግቶ ነበር።ለሰዓትት በተከሰተዉ ችግር ምክንያት 2.4 ቢሊዮን ብር ከባንኩ ወጪ መደረጉን ወይም ወደሌላ ሒሳብ ቁጥር መዘዋወሩን ባንኩ አስታዉቋል

https://p.dw.com/p/4dwYv
ባንኩ 2.4 ቢሊዮን ብር አለአግባብ እንደወጣበት አስታዉቋል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥርዓት መዛባት ባጋጠመበት ወቅት ከባንኩ አለግባብ ገንዘብ ካወጡት መካከል የሐዋሳ ተማሪዎችም አሉበትምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

የንግድ ባንክ ገንዘብና ተማሪዎች

              

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲስተም ችግር ማጋጠሙን ተከትሎ በቂ ገንዘብ ሳይኖራቸው በርከት ያለ ብር  አዘዋዉረዋል የተባሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ ተጠይቀዋል።የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፈዉ አርብ የኮምፒዊተር ሥርዓት ችግር አጋጥሞት  የገንዘብ ወጪና  የዝዉዉር ሥርዓቱ ተናግቶ ነበር።ለሰዓትት በተከሰተዉ ችግር ምክንያት 2.4 ቢሊዮን ብር ከባንኩ ወጪ መደረጉን ወይም ወደሌላ ሒሳብ ቁጥር መዘዋወሩን ባንኩ አስታዉቋል።አብዛኛዉን ገንዘብ ያወጡ ወይም ያዘዋወሩት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ናቸዉ።ከንግድ ባንክ አላግባብ ተዘዋውሯል ወይም ወጥቷል ሥለተባለዉ ገንዘብና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ሚና በተመለከተ የሐዋሳዉ ወኪላችን ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ የእዚያዉ የሐዋሳ  ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አነጋግሯል።

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ