የኑሮ ዉድነት በትግራይ
ረቡዕ፣ ግንቦት 3 2014ማስታወቂያ
በጦርነት እና እገዳ ከሌላዉ የኢትዮጵያ ክፍል በተገለለችዉ ትግራይ አለቅጥ የናረዉ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ የሕዝቡን ኑሮ እያቃወሰዉ መሆኑ ተዘገበ።የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለ ስሳሌ እንደዘገበዉ መቀሌ ዉስጥ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ 5 ብር ይሸጥ የነበረዉ 50 ግራም ዳቦ (ፉርኖ) ሰሞኑን 8 ብር ገብቷል።የፉርኖ ዱቄት፣የጤፍ፣ የበርበሬና የመሰል የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ሲጨምር ማኮሮኒና ፓስታን የመሳሰሉ የፋብሪካ ምርቶችን ገበያ ላይ ማግኘት ሲበዛ ከባድ ነዉ።የዚያኑ ያክል እዚያዉ ትግራይ የሚመረቱ እንደ ሽንኩርትና ቲማቲም የመሳሰሉ ማጣፈጫዎች ዋጋ ብዙ ለዉጥ አላሳየም።የከብትና የስጋ ዋጋ ግን ቀንሷል።
ሚሊዮን ኃይለ ስሳሌ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ