1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት አንድምታ

ረቡዕ፣ ኅዳር 22 2014

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ ኢትዮጵያ በሰሜን የአገሪቱ ክፍል እየተካሄደ ባለው ጦርነት የዓለም መነጋገሪያ በሆነችበት ባሁን ወቅት አገሪቱን ከጎበኙ የውጪ ከፍተኛ ባለሥልጣን ተጠቃሽ ናቸው።

https://p.dw.com/p/43hgP
Äthiopien China Außenminister Wang Yi
ምስል Seyoum Getu/DW

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ ከኢትዮጵያው አቻቸው ደመቀ መኮንን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተገለፀ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የቻይናውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይን ከቦሌ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር ሆነው ከተቀበሉ በኋላ ገንቢ ያሉትን ውይይት ማድረጋቸውን ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ ኢትዮጵያ በሰሜን የአገሪቱ ክፍል እየተካሄደ ባለው ጦርነት የዓለም መነጋገሪያ በሆነችበት ባሁን ወቅት አገሪቱን ከጎበኙ የውጪ ከፍተኛ ባለሥልጣን ተጠቃሽ ናቸው። ስለ ቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጉብኝት ለዶይቼ ቬለ አስተያየት የሰጡት የፖለቲካና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተንታኝ ጉብኝቱ ባለብዙ አንድምታ ነው ብለውታል።

ስዩም ጌቱ 

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ