1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቻይናዉ ፕሬዚዳንት ኮሮና በተዛመተበት ከተማ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 1 2012

ቻይና ኹዋን ዉስጥ የኮሮና ተኅዋሲ መዛመት ከታወቀ በኋላ የቻይናዉ ፕሬዚዳንት ሺን ፒንግ ወደ ኹዋን ከተማ ተጓዙ። በከተማዪቱ እና በሁባይ ግዛት የኮሮና ተሐዋሲ መዛመት «በመሠረቱ ተቀልብሷል» ብለዋል ፕሬዚደንቱ። የቻይና መንግሥት የዜና አገልግሎት ዢንዋ እንደዘገበዉ ፕሬዚዳንት ሺን ፒንግ ወደ ኹዋን ሁባይ ግዛት ያቀኑት በአዉሮፕላን ነዉ።

https://p.dw.com/p/3ZAtV
China Coronavirus Xi Jinping besucht Wuhan
ምስል picture-alliance/Xinhua/Xie Huanchi

ቻይና ኹዋን ዉስጥ የኮሮና ተኅዋሲ መዛመት ከታወቀ በኋላ የቻይናዉ ፕሬዚዳንት ሺን ፒንግ ወደ ኹዋን ከተማ ተጓዙ። በከተማዪቱ እና በሁባይ ግዛት የኮሮና ተሐዋሲ መዛመት «በመሠረቱ ተቀልብሷል» ብለዋል ፕሬዚደንቱ። የቻይና መንግሥት የዜና አገልግሎት ዢንዋ እንደዘገበዉ ፕሬዚዳንት ሺን ፒንግ ወደ ኹዋን ሁባይ ግዛት ያቀኑት በአዉሮፕላን ነዉ። ፕሬዚዳንቱ በሁባይ ወረዳ የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭትን ለመግታት እየተካሄደ ያለዉን እንቅስቃሴ ይቃኛሉ ተብሎአል። የኮሮና ተኅዋሲ በቻይና በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑ ከተነገረበት ካለፈዉ ጥር ወር ጀምሮ ፕሬዚዳንት ሺን ፒንግ በተለያዩ ቦታዎች የሚያደርጉትን ጉብኝት መቀነሳቸዉን የቻይና ብዙኃን መገናኛ አልሸሸጉም። ይህ በእንዲህ እንዳለ በቻይናዋ ግዛት ሁባይ በኮረና ተኅዋሲ ምክንያት ተደንግጎ የነበረዉ የመንቀሳቀስ መብት ከአንድ ወር ተኩል በኋላ ቀለል ማለቱ ተመልክቶአል። የሁባይ ግዛት አስተዳደር ዛሬ ይፋ እንዳደረገዉ፤ በተኅዋሲዉ ያልተያዙ ዜጎች እስከ ማዕከላዊ ግዛት ድረስ መንቀሳቀስ ይችላሉ። በጉዞ ላይ ያሉት በተኅዋሲዉ ያልተለከፉ ዜጎች መሆናቸዉን ለመለየት መንግሥት አንድ የኮምፒዉተር መለያ አፕሊኬሽን ይፋ ማድረጉን አሳዉቋል። ከዚህ ሌላ ግለሰቦች በተኅዋሲዉ የመያዝ አደጋ ምን ያህል ሊሆን እንደሚችል ለመለየት የሚያነግቡት የተለያዩ ቀለማት እንደሚሰጣቸዉ ተነግሮአል።

China Wuhan Besuch Präsident Xi Jinping
ምስል picture-alliance/Xinhua/X. Huanchi

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ