1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቻይና እና የአፍሪቃ ትብብር

ቅዳሜ፣ ጳጉሜን 2 2016

የቻይና እና የአፍሪቃ ትብብር (FOCAC) የላቀ እመርታ በማሳየት ላይ ነው ። የቻይና እና አፍሪቃ የትብብር ጉባኤ ትናንት ሲጠናቀቅ ቻይና ለአፍሪቃ 51 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ መመደቧ ተሰምቷል ። ቻይና ከኢትዮጵያ ጋ በመተባበር ፖለቲካዊ የእርስ በርስ መተማመንን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ ወዳጅነትን ለማጎልበት እንደምትሠራ ገልጣለች ።

https://p.dw.com/p/4kNSF
China Afrika Forum
ምስል Zhai Jianlan/picture alliance/Xinhua News Agency

የቻይና እና አፍሪቃ ትብብር ጎልብቷል

የቻይና እና የአፍሪቃ ትብብር (FOCAC)  የላቀ እመርታ በማሳየት ላይ ነው ። የቻይና እና አፍሪቃ የትብብር ጉባኤ ትናንት ሲጠናቀቅ ቻይና  ለአፍሪቃ 51 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ መመደቧ ተሰምቷል ። እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2000 የተመሰረው የቻይና እና አፍሪቃ የትብብር መድረክ  ላይ የተሰማው የድጋፍ ዜና ለ1 ሚሊዮን ሰዎች የሥራ እድል ይፈጥራልም ተብሏል ። 

ከ50 በላይ የአፍሪቃ መሪዎች እና ተወካዮች የተገኙበት የሦስት ቀናቱ ጉባኤ ዐርብ ተጠናቋል ።  ጉባኤው የተጠናቀቀው በስኬት መሆኑ ተገልጧል ።  በእርግጥም ቻይና በጉባኤው ወቅት ከ30 ሃገራት ጋ አንድም ሥልታዊ ትብብር መስርታለች አለያም ትብብሩን ከፍ አድርጋለች ። የቻይና ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባዪት ማዎ ኒንግ ።

ቻይና በጉባኤው ወቅት ከ30 ሃገራት ጋ ሥልታዊ ትብብር አጠናክራለች

«ይህ ጉባኤ ቻይና እና አፍሪቃ በጋራ ለማደግ ቁርጠኛ ስለመሆናቸው ጠንካራ መልእክት አስተላልፏል ጉባኤው በደቡባዊ የዓለም ንፍቀ ክበብ  ያሉ ሃገራት ለአብሮነት እና ትብብር ያላቸውን ጽኑእ እምነት ያሳየ ነው ለሰው ልጅ የወደፊት የጋራ ተጠቃሚነት ያለው ማኅበረሰብ  በመገንባቱ ረገድ የደቡባዊ የዓለም ንፍቀ ክበብ  ሃገራት ሚናን አጉልቶ ዐሳይቷል »

ቻይና እና አፍሪቃ በጋራ ዘመናዊነትን ለማፋጠን ስድስት ዋና ዋና ሐሳቦችን ይፋ አድርገዋል ። ትብብራቸውንም ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ የሚያስችል ዕቅድም ነድፈዋል ። ጉባኤው የቤጂንግ ስምምነት እና የድርጊት መርኃ ግብር አጽድቋል። የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ቺንፒንግ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ከአፍሪቃ ጋ ዘመናዊነትን በጋራ ለማራመድ 10 የትብብር የድርጊት መርኃ ግብሮችን ይፋ ማድረጋቸውንም ቃል አቀባዩዋ ዐሳውቀዋል ።

የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ቺንፒንግ እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ ጋ ቤጂንግ ውስጥ
የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ቺንፒንግ እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ ጋ ቤጂንግ ውስጥምስል Yin Bogu/Xinhua/IMAGO

የአፍሪቃ እና ቻይና ትብብር ከፍ ብሏል

የቻይና ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች ጋ በጉባኤው ወቅት በቅርበት ለመነጋገር መቻላቸው ተዘግቧል ። የቻይና ጠቅላይ ሚንሥትር ሊ ሺያንግ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ ጋ ቤጂንግ ውስጥ ሐሙስ ዕለት ፊት ለፊት ተገናኝተው ተነጋግረዋል ።

ቻይና  ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ፖለቲካዊ የእርስ በርስ መተማመንን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ ወዳጅነትን ለማጎልበት እንደምትሠራ የቻይናው ጠቅላይ ሚንሥትር ተናግረዋል ። ብሎም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ትብብር ለማስፋት እና ከኢትዮጵያ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ የላቀ እድገት ለማስመዝገብ እንደምትገፋበትም አክለዋል ሲል አሶሺየትድ ፕሬስ አትቷል ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ