1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ ሲቪክ ማኅበራት ጥሪ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 15 2016

ከ70 በላይ ነፃ ሲቪል ማሕበራዊ ያቀፈው የትግራይ ሲቪክ ማሕበረሰብ ተቋማት ሕብረት እንደሚለው፥ በጦርነቱ ወቅት በትግራይ ለተፈፀሙ እንዲሁም አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች እየተፈፀሙ እየቀጠሉ ነው ላላቸው የመብት ጥሰቶች እና የጦር ወንጀሎች በአለምአቀፋዊ እና ገለልተኛ ወገን ሊጣሩ፣ ፍትህ እንዲሁም ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል ።

https://p.dw.com/p/4Y4mE
መቀለ ከተማ
መቀለ ከተማ ምስል EDUARDO SOTERAS/AFP

በትግራይ ለተፈፀሙ የመብት ጥሰቶች እና የጦር ወንጀሎች በአለም አቀፋዊ እና ገለልተኛ ወገን ሊጣሩ፣ ፍትህ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል።

በጦርነቱ ወቅት ለተፈፀሙ የመብት ጥሰቶች እና ወንጀሎች ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል ሲሉ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ሲቪክ ማሕበራት ጥሪ አቀረቡ። በጦርነቱ ዓለምአቀፍ ይዘት ያላቸው ወንጀሎች መፈፀማቸው የሚያነሳው የትግራይ ሲቪክ ማሕበረሰብ ሕብረት የተባለ ተቋም በበኩሉ ዓለምአቀፋዊ፣ ገለልተኛ ማጣራት ሊደረግበት ይገባል ብሏል። በትግራይ የቀጠለው የመናገር ነጻነት ዓፈናለሁለት ዓመታት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተደረገው ደም አፋሳሽ ጦርነት በርካታ የመብት ጥሰቶች እና ዓለምአቀፍ ወንጀሎች የተፈፀሙበት እንደሆነ የመብት ተሟጓች ድርጅቶች እና መርመሪ አካላት ሲገልፁ ቆይተዋል። ከጦርነቱ መቆም በኃላ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ አፍሪካ ሕብረት እና ሌሎች አካላት ይደረጉ የነበሩ ምርመራዎች መቆማቸው አሳሳቢ እንደሆነ የሚገልፁ አካላት፥ ለተፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂነት ካልተረጋገጠ ለሌላ እልቂት በር መክፈት፣ የሕግ የበላይነት መጣስ መሆኑ በማንሳት ይወቅሳሉ። ከ70 በላይ ነፃ ሲቪል ማሕበራዊ ያቀፈው የትግራይ ሲቪክ ማሕበረሰብ ተቋማት ሕብረት እንደሚለው፥ በጦርነቱ ወቅት በትግራይ ለተፈፀሙ እንዲሁም አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች እየተፈፀሙ እየቀጠሉ ነው ላላቸው የመብት ጥሰቶች እና የጦር ወንጀሎች በአለምአቀፋዊ እና ገለልተኛ ወገን ሊጣሩ፣ ፍትህ እንዲሁም ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ሲል ይገልፃል።በትግራይ የ3 ቀናት ክልላዊ ሃዘን ታወጀ

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ተፈጽመዋል የሚባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመመርመር ያቋቋመው ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ኮሚሽን የመጨረሻውን ሪፖርት ጥቅምት 2 ቀን 2016 ይፋ አድርጎ የስራ ግዜው እንዳበቃ ይታወቃል።
የትግራይ ሲቪክ ማሕበረሰብ ተቋማት ሕብረት ስራ አስከያጅ አቶ ያሬድ በርሃ ለዶቼቬለ እንደገለፁት፥ የተፈፀሙ ወንጀሎች በሀገር ውስጥ ባሉ ተቋማት ለማጣራት እና ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ተአማኒነት የሚጎድለው ያደርገዋል ይላሉ። ምስል Million Haileselassie/DW

የትግራይ ሲቪክ ማሕበረሰብ ተቋማት ሕብረት ስራ አስከያጅ አቶ ያሬድ በርሃ ለዶቼቬለ እንደገለፁት፥ የተፈፀሙ ወንጀሎች በሀገር ውስጥ ባሉ ተቋማት ለማጣራት እና ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ተአማኒነት የሚጎድለው ያደርገዋል ይላሉ።የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ተፈጽመዋል የሚባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመመርመር ያቋቋመው ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ኮሚሽን የመጨረሻውን ሪፖርት ጥቅምት 2 ቀን 2016 ይፋ አድርጎ የስራ ግዜው እንዳበቃ ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግስት ተፈፀሙ የተባሉ ወንጀሎች እና የመብት ጥሰቶች በሽግግር ፍትህ ፖሊሲ እንደሚያየው ሲገልፅ ቆይቷል። በፍትህ እና ተጠያቂነት ጉዳዮች አስተያየታቸው የጠየቅናቸው የትግራይ ፖለቲከኞችም በጦርነቱ ወቅት ለተፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል ይላሉ። የዓረና ትግራይ ሊቀመንበር አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ "ተጠያቂነት አለማረጋገጥ ለቀጣይ ወንጀል ሁኔታ ማመቻቸት ነው" ብለዋል። ድርቅ በትግራይ
ሌላው ሀሳባቸው ያጋሩን የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ህዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ ሃይለአብ ሃይለስላሴ በበኩላቸው "እኛ በትግራይ የተፈፀመው ዘር የማጥፋት ወንጀል ነው ብለን ነው የምንገልፀው። ለዚህ ደግሞ ፍትህ ሊረጋገጥ የሚችለው ዓለምአቀፍ እና ገለልተኛ የወንጀል አጣሪ ሲመረምረው እና ብይን ሲሰጥበት ነው። በተጨማሪም በጦርነቱ እና ወንጀሎቹ ድንበር ተሻግረው የገቡ ሐይላትም ተሳትፈዋል።ስለዚህ አለምአቀፋዊ መልክ አለው ብለን ነው የምናምነው" ብለዋል። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር፥ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት የቀረበው የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ማሻሻያ እንዲደረግበት በቅርቡ ለፍትህ ሚኒስቴር መጠየቁ ይታወሳል። በዚህ የፍትህ እና ተጠያቂነት ጉዳይ ከፍትህ ሚኒስቴር ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለግዜው አልተሳካም።

ሚሊዮን ኤይለ ሥላሴ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ