1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የበዓል ግብይት በአዲስ አበባ

እሑድ፣ ሚያዝያ 11 2012

በፋሲካ በዓል ዋዜማ በአዲስ አበባ አያት አደባባይ የተለያዩ የእርድ እንስሶች ለግብይት ቀርበው እና ገበያውም እንደወትሮው ሁሉ በተሟሟቀ ሁኔታ ሲከናወን ተስተውሏል። ይሁንና ግብይቱ ከእስከዛሬው የተቀዛቀዘ መሆኑን ሻጮችም ገዥዎችም ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3b950
Äthiopien | Ostern Markt in Addis Abeba
ምስል DW/S. Muchie

በዚሁ የገበያ ስፍራ በሬ፣ ፍየልና ዶሮን ጨምሮ በርከት ያሉ በጎች ለሽያጭ ቀርበዋል። ይሁንና ግብይቱ ከእስከዛሬው የተቀዛቀዘ መሆኑን ሻጮችም ገዥዎችም ተናግረዋል። በተለይ የበግ እና ፍየል ሽያጭ ላይ የዋጋ ጭማሪ መስተዋሉንና በአንጻሩ የበሬ እና ዶሮ ዋጋ በመጠኑም ቢሆን ቅናሽ እንዳለው የአዲስ አበባው ዘጋቢ ሰለሞን ሙጬ ያነጋገራቸው ሸማቾች ገልጸዋል። የግብይት ሂደቱ ግን የኮሮና ተኅዋሲ ከአንዱ ወደ ሌላው ለመተላለፍ አመቺ በሆነና በሚያጋልጥ ፣ የተሰጡ መመሪያዎች ሁሉ ችላ በተባሉበት አኳኋን ሲከናወን ተመልክተናል። ከቅዳሜ ረፋዱ ጀምሮ በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውረን ባደረግነው የበዓል ዋዜማ ግብይት ትልልቅ የህንጻ የገበያ ማዕከላት ጭር ብለዋል።በድምጽ ማጉያ ይታገዙ የነበሩ የግብይት ጥሪዎች የሉም። የሰው ውር ውርም በእጅጉ ቀንሷል።

Äthiopien | Ostern Markt in Addis Abeba
ምስል DW/S. Muchie

በ እርድ እንስሳት ይሞሉ የነበሩ ዋና ዋና መንገዶች ክፍት ሆነው ተስተውለዋል። በአጠቃላይ ግን በኮሮና ተህዋሲ ስጋት እና ይህንንም ተከትሎ መረርሽኙን ለመከላከል በወጡ የመንግሥት ከልካይ መመሪያ እና ደንቦች የተነሳ በከተማዋ የ2012 ዓም የትንሳኤ በዓል ግብይት ተቀዛቅዞ ተስተውሏል።
ሰለሞን ሙጩ 
ልደት አበበ