የትንሳኤ በዓል አከባበር በኦርቶዶክስ እና ካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት
እሑድ፣ ሚያዝያ 16 2014ማስታወቂያ
በክርስትና እምነት አማንያን ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት የፋሲካ ወይም የትንሣኤ በዓል ዛሬ እየተከበረ ነው።
ትናንት በትንሣኤው ዋዜማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት አብያተ ክርስትያናት በተለይም የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት በተዋበ መንፈሳዊ ክዋኔ ከምሽቱ ሦስት እስከ ሌሊቱ አሥር ሰዓት ተፈፀማል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አዲስ አበባ ጉድር ሾላ በሚገኘው ሰዓሊተ ምህረት ቤተ ክርስቲያን እና ጎሮ አካባቢ በሚገኘው በአዲስ አበባ አገረ ስብከት የቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ቤተክርስትያን የዋዜማው ምሽት እና ሌሊት ድምቀት በተሞላው መንፈሳዊ ሥርዓት ዋዜማው ትከብሯል።
ሰለሞን ሙጬ
እሸቴ በቀለ