1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትምሕርት ዘርፉ ሥርዓታዊ መፍትኄ ያሻዋል ተባለ

ሐሙስ፣ መጋቢት 29 2014

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ የመሥሪያ ቤታቸውን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርቡ ከአባላቱ ለተነሳላቸው በርከት ያሉ ጥያቄዎች ሲመልሱ የትምህርት ሥርዓቱ መሠረታዊ የግብረገብነት ክስረት ውስጥ ገብቷል ብለዋል።

https://p.dw.com/p/49cgT
Äthiopien Parlament Addis Abeba
ምስል Solomon Muche/DW

ዘርፉ ከእየ አካባቢነት ፉክክርም ሊለይ ይገባል

የኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ ሥርዓታዊ ችግር ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ ሥርዓታዊ መፍትኄ ያስፈልገዋል ሲል የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ተናገረ። የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ የመሥሪያ ቤታቸውን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርቡ ከአባላቱ ለተነሳላቸው በርከት ያሉ ጥያቄዎች ሲመልሱ የትምህርት ሥርዓቱ መሠረታዊ የግብረገብነት ክስረት ውስጥ ገብቷል ብለዋል። ይህንን ለማስተካክልም ትምህርት እና ፖለቲካ ሊለዩ፣ ዘርፉ ከእየ አካባቢነት ፉክክርም ሊለይ ይገባል ብለዋል። የብዙ ትማሪዎችን ሕይወት መጉዳቱ በስፋት የመወያያ ርእስ የሆነው የዘንድሮ  የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመግቢያ ፈተና ጉዳይም ጥያቄ ተነስቶበት ነበር። 
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ