1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታንዛንያ የአካባቢ ምርጫዎች ውጤትና ፕሬዝዳንት ሳሚያ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 28 2017

ተቃዋሚዎች ለሚፈጸምባቸው ጥቃትና ወከባ ተጠያቂው የቻማ ቻማ ማፑንዱዚ ፓርቲ ነው ይላሉ። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም በዚህ ሰበብ ታንዛንያን እያገለለ ነው። ታዛቢዎችና ተቃዋሚዎች እንደሚሉት ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲመጣ ታንዛንያ በአንድ ፓርቲ ስርዓት ትመራ በነበረበት በ1977 የጸደቀው የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት መሻሻል አለበት።

https://p.dw.com/p/4ns1b
Tansania Sansibar Präsidentin Samia Suluhu Hassan bei Kizimkazi Festival
ምስል Presidential Press Service Tanzania

የታንዛንያ የአካባቢ ምርጫዎች ውጤትና ፕሬዝዳንት ሳሚያ

ባለፈው ሳምንት በተካሄደው በታንዛንያ አካባቢያዊ ምርጫዎች ይፋ ውጤት መሠረት የታንዛንያ ገዥ ፓርቲ ቻማ ቻማ ማፑንዱዚ ከ98 በመቶ በላይ መቀመጫዎችን አሸንፏል። በምህጻሩ CCM ተብሎ የሚጠራው ፓርቲው በምሥራቅ አፍሪቃዊቷ ሀገር ፖለቲካ ገዝፏል። የዛሬ ሳምንቱ ምርጫም ከጥቅምት 2025ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፊት ለታንዛንያ ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ፈተና ሆኖ ታይቷል። የታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሳምያ ሱሉሁ የህዝብ ድጋፍም በምርጫው ለመጀመሪያ ጊዜ  የተፈተነበትም ሆኗል። ውጤቱ የዛሬ ሦስት ዓመት የጋናው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ሲሞቱ ሥልጣን ለያዙት ለ64 ዓመቷ የታንዛንያዋ መሪ ሱሉሁ አስደናቂ ስኬት ተብሏል።

የታንዛንያ ምርጫ እና ዉዝግቡ  
ዳሬሰላም በሚገኘው በዶክተር ሳሊም አህመድ ሳሊም የውጭ ጉዳዮች ማዕከል በመምህርነት የሚሰሩት ጎድዊን ግኖዴ አንድዌ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ትልቁ ድል፣ CCM በታንዛንያ ፖለቲካ ውስጥ ላለፉት 60 ዓመታት ገዝፎ መዝለቁን የሚያመለክት ነው። እርሳቸው እንዳሉት ገዥው ፓርቲ  ሌሎች ፓርቲዎች የምርጫ ዘመቻ ማካሄድ በማይችሉበትና አነስተኛ ደጋፊ ባላቸው በገጠር አካባቢዎች ከነርሱ የተሻለ እድል አለው። ከዚህ ሌላ ፓርቲው ለምርጫው ብዙ ገንዘብም አውጥቷልም።


ድምጽ መስጫውን ቀን ሲቃረብ ተቃዋሚው ፓርቲ ቻዴማ አንዳንድ እጩ ተወዳዳሪዎቹ ከምርጫው እንዲሰረዙ መደረጉን ትክክለኛ አይደለም ሲል ተቃውሟል። ከዚህ በተጨማሪም ከአካባቢ ምርጫ ጋር በተያያዙ ክስተቶች ሦስት አባላቶቼ ተገድለውብኛልም ሲል አስታውቋል። ባለሥልጣናትንም ምርጫውን በማጭበርበር ከሷል። የመብት ተሟጋች ቡድኖች እና ምዕራባውያን መንግሥታትም በተቃዋሚ ፖለቲከኞች ልይ የሚደረግ ጫና ፣ተደጋጋሚ እሥር ፣እገታና ግድያ እንደሚፈጸምባቸው ጠቁመዋል። በዚህ ሳምንት ሰኞ የታንዛንያ ተቃዋሚ ወጣቶች መሪ አብዱል ኖንዶ መታገቱ ከተሰማ በኋላ ዳሬሰላም በሚገኝ የባህር ዳርቻ  ተጥሎ ተገኝቷል።በወቅቱም ክፉኛ ቆስሎ ነበር የተገኘው።  በታንዛንያ የሚፈጸመውን ይህን መሰሉን ጥቃት የታንዛንያ  ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አውግዛለች። ቤተ ክርስቲያኗ ወቅቱን በህመምና ሰቆቃ የተሞላ የሙከራ ጊዜ ብላዋለች። 


ተቃዋሚዎች ለዚህ ሁሉ ጥቃት ተጠያቂው የቻማ ቻማ ማፑንዱዚ ፓርቲ ነው ይላሉ። ፕሬዝዳንት ሱሉሁንም ተጠያቂ የሚያደርጉ ጥቂት አይደሉም። በዶዶማ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር  ኮንራድ ጆን ማሳቦ እንደሚሉት ግን ተጠያቂዋ ሳምያ ብቻ ሊሆኑ አይችሉም ። ይልቁንም የተቋሞቻቸው አወቃቀር እንጂ ይላሉ። 
«ሱሁሉን በተመለከተ የተቋማቱ ተወካይ ቢሆኑም ሳምያን እንደ ግለሰብ ማየት የለብንም። ከዚያ ይልቅ አጠቃላዩን ስርዓት ነው መመልከት ያለብን። ችግሩ እርሳቸው ብቻ ሊሆኑ አይችሉም። ምርጫውን የሚመራው ማዕቀፍና የታንዛንያ ዴሞክራቶችም ይመለከታቸዋል። እስካሁን ያልተቀየሩትና አሁን ያለው ገዥ ፓርቲ በ1992 ወደ ብዝሀ ፓርቲ ስንቀየር በአወቃቀሩ CCM ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለየ የበለጠ ነጻነት ተስጥቶት ነበር። ታዲያ መጀመሪያ ላይ ሳምያ ከቀድሞው መሪ በተለየ ይህን ለመቀየር ምልክት ታይቶ ነበር።»   

የታንዛንያ አካባቢያዊ ምርጫ
የታንዛንያ አካባቢያዊ ምርጫምስል Eric Amos/DW

ታንዛንያ፤ አዲስዋ ፕሬዚዳንት ቃለ-መኃላ ፈፀሙ

ማሳቦ ሌሎች ታዛቢዎችና ተቃዋሚዎች እንደታዘቡት በታንዛንያ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲመጣ  ታንዛንያ በአንድ ፓርቲ ስርዓት ትመራ በነበረበት በ1977 የጸደቀውና ለዓመታት እንዳለ የቆየው የታንዛንያ ሕገ መንግሥት መሻሻል አለበት። «ስለዚህ አንዱ ልንመለከተው የሚገባ ጉዳይ የታንዛንያን የፖለቲካ መድረክ ሊያሰፉ ይችሉ የነበሩ ዋና የሚባሉ ለውጦችን ወደ ደንቦች መቀየር ችለዋል ወይስ አልቻሉም የሚለው ነው።ከዚያ ይልቅ የገቡትን ቃል ብቻ የምንመለከት ከሆነ ብዙ ቃል የገቧቸው ጉዳዮች አሉ። ይህን ምርጫ ለማካሄድ የሚያግዝ ደንብ ስስንመለከት በዚህ ረገድ በሕግ ማዕቀፍ ደረጃ የተደረገው ጥቂት ነው።»
በ2019 ዓም ተቃዋሚው ፓርቲ ጥቃትና ወከባን ምክንያት አድርጎ ከምርጫው ራሱን አገለለ። ይህም CCM የምክር ቤት መቀመጫዎችnne በሙሉ እንዲወስድ መንዱን ጠረገለት። ሆኖም ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በፖለቲካው መድረክ እንዳይሳተፉ አቅማቸውን ለማዳከም ያደረጉት ጥረት ብዙ ዋጋ አስከፍሏቸዋል። በተደጋጋሚ ከምዕራባውያን አጋሮቻቸው ጋር ባለመስማማታቸው በታንዛንያ ዓለም ዓቀፍ ኢንቬስትመንት ቆመ። ማጉፉሊ ሞተው ሱሉሁ ሀሰን ፕሬዝዳንት ሲሆኑ ደግሞ በማጉፉሊ ዘመን በተቃዋሚዎችና በታንዛንያ መገናኛ ብዙሀን ላይ የተጫኑት ጨቋኝ ገደቦች ገሸሽ ሲሉ የፖለቲካ ታዛቢዎች ፕሬዝዳንቷን ማወደስ ጀመሩ። ተንታኝ አማኒ እንደተናገሩት ሳምያ ሥልጣን ሲይዙ ለመቻቻልና እርቅ ጥሪ አቅርበው ተቃዋሚዎችን በፖለቲካውው መድረክ የመሳተፍ እኩል እድል እንዲያገኙ ለማሳየት ሞክረዋል። በዚህ መነጽር ሲታይ ታዲያ ሳምያ ዴሞክራሲን በተመለከተ ከማጉፉሊ የተሻለ ሰርተዋል ብለዋል።  

ታንዛንያ የመጀመርያዋን ሴት መከላከያ ሚኒስትር ሾመች
በመስከረም ወር የአውሮጳ ኅብረት ሚስዮን ሃላፊና ፣የብሪታንያ፣ ካናዳ ፣ኖርዌይ ፣እና የስዊስ ኤምባሲዎች በቅርቡ ስለተዘገበው ታንዛንያ ውስጥ በሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪዎች ላይ የሚፈጸም ጥቃት ሰዎችን መሰወር እና ሞት የጋራ መግለጫ አውጥተው ነበር። በምላሹም ፕሬዝዳንት ሳምያያ ሱሁሉ ሀሰን ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ ምዕራባውያን ሀገራትን የታንዛንን የሀገር ውስጥ ጉዳዮች አያያዝ በመተቸታቸው ወቅሰዋቸው ነበር። ሱሉሁ  በቅርቡ ሪዮ ደጀኔሮ በተካሄደው የቡድን ሀያ ጉባኤ ላይ ሀገራቸውን ወክለው ተሳትፈዋል። ሱሉሁ ይህን መሰሉን ጥረት ያጠናከሩት ታንዛንያ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከተገለለች በኋላ ነበር። 

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ